
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ይዞታ እንደሚያሳስባቸው መግለጻቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገበ። የጉተሬሽን መግለጫ የጠቀሰው ዘገባ አክሎም፣ ዋና ጸሐፊው በክልሉ የሲቪሎችን ችግር ለማቅለል የኢትዮጵያ መንግሥት ከተመድ ጋር በትብብር መሥራቱ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት መስጠታቸውንም ጠቅሷል። በተጨማሪም ዘገባው የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በዛሬው ዕለት በዚሁ ጉዳይ ለመነጋገር ስብሰባ እንደሚያካሂድ ዲፕሎማቶች እንደገለጹም አመልክቷል።…
Read More →