Category: ዜና

“ከመድረክ የወጣነው ኦፌኮ ከመድረክ ሕግ ውጭ እየሠራ ስለሆነ ነው” ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ
By: Date: February 8, 2021 Categories: ዜና

ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ በተደረጉ ምርጫዎች ላይ የተሳተፉት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ብዙ ፓርቲዎችን አቅፎ የነበረው የመድረክ መሪ ነበሩ፡፡የአ ዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጅ ምሁሩ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ስማቸው ከሚነሳ ፖለቲከኞች መካከል የመጀመሪው ረድፍ ላይ እንደሚቀመጡም ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ’ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በምርጫ 2013 ከመድረክ ጋር ስላላቸው እሰጥ አገባ ፣ ስለብሔራዊ…

Read More →
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑክ ወደ ትግራይ ክልል አቀና
By: Date: February 8, 2021 Categories: ዜና

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችንና መማክርትን ያካተተ ልዑክ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየትና ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል ማቅናቱን የጉባኤው ዋና ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለጹ። ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎች መማክርትን ያካተተ ልዑክ ወደ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ማቅናቱ ነው የተጠቀሰው። ልዑኩ…

Read More →
የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ከፈጠረው የሃሰት ሥነ ልቦና ጋር እራሱን አገናኝቶ የነበረ በመሆኑ ከፍ ያለ ኀዘን ውስጥ መግባቱ አይቀርም – አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ
By: Date: February 8, 2021 Categories: ዜና

የትግራይ ሕዝብ ከሕግ ማስከበር ዘመቻው በፊት የተለያየ የሥነ ልቦና ጫናዎች ሲደርሱበት እንደነበር የኢሳት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አመለከቱ፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳመለከቱት፣ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የትግራይ ሕዝብ ከሕግ ማስከበር ዘመቻው በፊት የተለያዩ የሥነ ልቦናዊ ጫናዎች ሲደርሱበት የኖረ ነው። ለረጅም ዘመን ወያኔዎች ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የትግራይንም ሕዝብ ትክክል ባልሆነ መንገድ…

Read More →
ወደ ጎንደር፤ላልይበላ እና ባህርዳር የነበሩ የአገር ውስጥ በረራዎች በአየር ንብረት መበላሸት ምክንያት ተስተጓጎሉ
By: Date: February 8, 2021 Categories: ዜና Tags:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የአገር ውስጥ በረራዎች መስተጓጎሉን አስታውቋል። አየር መንገዱ እንዳስታወቀው በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ ጥር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ላልይበላ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር ይደረጉ የነበሩ በረራዎች ተስተጓጉለዋል ብሏል። የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሰን በረራውን እንደሚቀጥል አየር መንገዱ ገልጿል።…

Read More →
ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ዓመታት ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሰባት ውሀማ ስፍራዎች የውሀ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደምታስጀምር አስታወቀች
By: Date: February 8, 2021 Categories: ዜና

ሀገሪቷ አሁን ያሉት እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ይሰራሉ ቀድመው ስራ የጀመሩት ደግሞ በተሻለ ቴክኖሎጂ ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል። በ10 አመቱ መሪ የትራንስፖርት የልማት እቅድ ውስጥ ከተቀመጡ ጉዳዮች መካከል የውሀ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ይገኝበታል፡፡ በዚህም በጣና ሀይቅ፣ ባሮ ወንዝ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ ተከዜ፣ ህዳሴ ግድብ እና በጊቤ የውሀ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ለማልማት ታቅዶ ስራ…

Read More →
የኮንዶሚኒየም ግንባታ የፋይናንስ ጉዳይ ቢታይ ከዚህ በላይ ጉድ ሊኖር ይችላል – የኮንዶሚኒየም ጥናት ቡድን አስተባባሪ
By: Date: February 8, 2021 Categories: ዜና

የጋራ ቤቶች ልማት የፋይናንስ ጉዳይ ላይ ፍተሻ ቢደረግ ከማስተላለፉ ጋር በተያያዘ በጥናት ከተገኘው ችግር በላይ ጉድ ሊኖር እንደሚችል በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ልማት መምህር እና የኮንዶሚኒየም ጥናት ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ቱሉ ቶላ አስታወቁ። 400 ሕንፃዎች ግንባታ ፈጽሞ እንዳልተካሄደም አስታወቁ። ዶክተር ቱሉ በጉዳዩ ዙሪያ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በሆነው ነገር ሁላችንም ግራ ተጋብተን ነበር፡፡…

Read More →
የኢትዮጵያና የዓለም ምግብ ድርጅት ስምምነት
By: Date: February 8, 2021 Categories: ዜና

የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ለተጎዳዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ለመሰጠት ተስማሙ። የዓለም ምግብ ድርጅት የበላይ ዴቪድ ቤስሌይ የትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ከጎበኙ በኋላ ትናንት እንዳሉት ድርጅታቸዉ ሠብአዊ ርዳታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር «በተጨባጭ ርምጃዎች» ላይ ተስማምቷል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የቤስሌይን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ዓለም አቀፉ ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት የሌለባቸዉ አካባቢዎችን ጨምሮ…

Read More →
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ፊቤላ የዘይት ፋብሪካን መረቁ
By: Date: February 7, 2021 Categories: ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት የማምረት አቅም ያለውን ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ መረቁ፡፡vየሀገሪቱን የምግብ ዘይት አቅርቦት 60 በመቶ የመሸፈን አቅም እንዳለው የተነገረለት ፊቤላ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከምግብ ዘይት ምርት በተጨማሪ የሰሊጥ ማቀነባበሪያ፣ ሳሙና እና የእንስሳት መኖ ያመርታልም ነው የተባለው። በባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የተገነባው ፋብሪካው 4 ነጥብ 5…

Read More →
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ።
By: Date: February 7, 2021 Categories: ዜና

በምረቃ ስነ ስርአት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎችም ከፍተኛ የፌደራል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።አራት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የቡሬ ኢንዱስትርያል ፓርክ ሥራው በመጀመሪያ ምእራፉ 260.5 ሔክታር መሬት ላይ አርፎ የውኃ፣ የመብራት እና ቴሌኮም መስመሮች እንዲሁም የመንገድ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ተሟልተውለታል።ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎች…

Read More →
የአህያ ቆዳ ገበያ
By: Date: February 7, 2021 Categories: ዜና

ከዕለት ወደ ዕለት እየተስፋፋ በመጣው የአህያ ቆዳ ፍላጎት ምክንያት፣ ከኢትዮጵያ በርካታ አህዮች በሕገወጥ መንገድ እንደሚወጡና የአገሪቱ አህዮች ቁጥር አደጋ ላይ መውደቁ ተገለጸይህ የተገለጸው ብሩክ ኢትዮጵያ የተባለው የጋማ ከብቶችን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚሠራ ዓለም አቀፍ ድርጅት፣ ሕገወጥ የአህዮች ግብይትን ስለ መከላከል የሚገልጽ የውይይት መድረክ ሐሙስ ጥር 27 ቀን 2013 በአዳማ ከተማ ባከናወነበት ወቅት ነው፡፡ በውይይቱ ላይ የመነሻ…

Read More →
በትግራይ ሕፃፅና ሽመልባ በተባሉ የስደተኞች መጠለያ የነበሩ ኤርትራውያን ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ
By: Date: February 7, 2021 Categories: ዜና Tags:

በትግራይ ክልል ሕፃፅና ሽመልባ በተባሉ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩ 20,000 የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች፣ መንግሥት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ሲያከናውን በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የመጠለያ ጣቢያዎቹን ለቀው እንደወጡ ተገለጸ፡፡ በክልሉ ሕፃፅ፣ ሽመልባ፣ ማይዓይኒና አደሃረሽ የተባሉ መጠለያዎች ውስጥ በአጠቃላይ ከ47,000 በላይ የኤርትራ ስደተኞች ይኖሩ እንደነበር፣ የስደትና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር…

Read More →
የግብፅ መንግሥት ኤርትራ ውስጥ የተያዙ ግብፃዊያን ዓሳ አጥማጆች እንዲለቀቁ የኤርትራን መንግሥት ጠየቀ
By: Date: February 7, 2021 Categories: ዜና Tags:

በአምስት ጀልባዎች በመሆን በኤርትራ የባህር ክልል ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የተገኙትን ግብፃዊያን የኤርትራ የባህር ኃይል በቁጥጥር ሥር ያዋለው ባለፈው ወር መሆኑን መረጃዎች የሚያመ ለክቱ ሲሆን፣ ዓሳ አጥማጆች ናቸው የተባሉትን ግብፃዊያን ለማስለቀቅም የግብፅ መንግሥት ኦፊሳላዊ ጥያቄ ለኤርትራ መንግሥት ማቅረቡ ተሰምቷል። የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ከኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳላህ ጋር በተጠናቀቀው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ባደረጉት የስልክ ውይይት፣…

Read More →
የሕወሃት መወገድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የተዘራውን የብሄር ክፍፍል መርዝ ይነቅላል – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
By: Date: February 6, 2021 Categories: ዜና

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሕወሃት መወገድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የተዘራውን የብሄር ክፍፍል መርዝ እንደሚነቅል ዛሬ ለፕሮጀክት ስንዲኬት በጻፉት መጣጥፍ ገልጠዋል፡፡ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በትግራይ ያለውን ስጋት እንደሚገነዘቡ የጠቀሱት ዐቢይ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ በትግራይ የሰላማዊ ሰዎችን ሰቆቃ መቅረፍ ቀዳሚው ትኩረታቸው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡…

Read More →
በጁንታው ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ 420 የህወሃት ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ እየተሰራ ነው
By: Date: February 6, 2021 Categories: ዜና Tags:

በጁንታው ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ 420 የህወሃት ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮችና 682 በወንጀል ድርጊት የተሳተፉ አባላት በህግ እንዲጠየቁ እየተሰራ ነው –ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጥር 29/ 2013 ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጁንታው ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ 420 የህወሃት ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች እንዲሁም 682 በወንጀል ድርጊት የተሳተፉ የጁንታው አባላት ላይ መረጃ በማሰባሰብ በህግ…

Read More →
የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን የዲ.አር.ኮንጎ ፕሬዝደንት ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ተረከቡ
By: Date: February 6, 2021 Categories: ዜና

በየዓመቱ ጥር መጨረሻና የካቲት መጀመሪያ የሚካደው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ ስብሰባ በዚህ ዓመት በተለየ መልኩ መካሄድ ጀምሯል፡፡ 34ኛው የመሪዎች ጉባዔ እንደወትሮው ሁሉ መሪዎችን በአካል ባያገናኝም የውይይት አጀንዳዎችን በመምረጥ በበይነ መረብ እየተካሄደ ነው፡፡ የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ስብሰባ ከሰሞኑ የተካሄደ ሲሆን የመሪዎቹ ጉባዔ ዛሬ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት የመሪዎቹ ጉባዔ ዛሬና ነገ ይካሄዳል፡፡ የሕብረቱ መሪዎች ስብሰባውን በአካል ያላደረጉበት ምክንያት…

Read More →
በሰላም ሚኒስትር የተመራ ልዑክ በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት መቐለ ገባ
By: Date: February 6, 2021 Categories: ዜና

በሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና በዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ የተመራ የልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት መቐለ ገብቷል። እንደ ኢዘአ ዘገባ የልዑክ ቡድኑ አባላት በትግራይ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በመቐለ እና በአካባቢው እንዲሁም በኩሃ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ሁኔታን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ። በተጨማሪም በትግራይ ክልል እየተሰጠ ባለው የሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ…

Read More →
የጁንታው ስህተት በታሪክ እንዳይደገም የሰራዊቱን የሕግ ማስከበር ተጋድሎ በየጊዜው ለሕዝብ ማቅረብ ይገባል – ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
By: Date: February 6, 2021 Categories: ዜና

የአጥፊውን ጁንታ ቡድን ስህተት በኢትዮጵያ ታሪክ እንዳይደገም የመከላከያ ሰራዊትን የሕግ ማስከበር ተጋድሎ በየጊዜው እያስታወሱ ለሕዝብ ማቅረብ እንደሚገባ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ አስታወቁ። ሜጀር ጄኔራል መሐመድ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀውን ዘመቻ ለፍትህ የፎቶግራፍ አውደርዕይ በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት የጁንታውን ቡድን አይነት በሃገር አንድነት እና መከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመው ጥፋት በታሪክ እንዳይደገም…

Read More →
የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ ነው
By: Date: February 6, 2021 Categories: ዜና

በኢትዮጵያ ከመንግስት እና ከግል ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን ማስረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ ነው። የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ይህ አሰራር ተቋማት እና ግለሰቦች ሰራተኞችን ለመቅጠር በሀሰተኛየትምህርት ማስረጃ እንዳይታለሉ ይረዳል። በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ሀሰተኛ እና የተሳሳተ የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ…

Read More →