Category: መንግስትና አስተዳደር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ
By: Date: November 11, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ሊቀመናብርት አንዷ የሆኑትን ሜሊንዳ ጌትስንጋር ተወያዩ። ፋውንዴሽኑ ኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነቷ እንዲጨምር እና ሰፊ የጤና ሽፋን እንዲኖራት ለበርካታ ዓመታት ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። በውይይታቸው ወቅትም ፋውንዴሽኑ የመንግሥት ዐበይት የትኩረት መስኮች ላይ አስተዋጾ የሚያደርግባቸው መንገዶች ላይ ምክክር አድርገዋል። ምንጭ፡-ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት

Read More →
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ አጋጥሞ የነበረውን ችግር ለተለዬ አጀንዳ ለማዋል የሚጠቀሙ አካላትን ዩኒቨርሲቲው አወገዘ፡፡
By: Date: November 11, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ 13 ተጠርጣዎች በቁጥጥ ሥር መዋላቸው ተገለጸ፡፡ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉንና የተወሰኑ ተማሪዎች መቁሰላቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አስናቀ ለአብመድ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከትናንት ጀምሮ በተረጋጋና በሠላማዊ ሁኔታ ይገኛል። ተማሪዎችም እንዲረጋጉ በየደረጃው ውይይቶች ተደርገዋል፤ ዛሬም እንደቀጠሉ ናቸው፡፡…

Read More →
ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለአማራ ክልል ምክር ቤት እንዲሆን ተወሰነ
By: Date: November 11, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር

የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 14ኛ በመደበኛ ጉባኤ ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለክልል ምክር ቤት እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል። የክልሉ ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና አስተዳደር ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ ሰጤ፥ ጥረት ኮርፓሬት ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሆን የተባለበትን ዝርዝር ሁኔታዎች አቅርቧል። በዚህም ጥረት ኮርፓሬት የክልሉ ህዝብ ሃብት መሆኑን፣ የአሰራር ግልፀኝነት ችግር የነበረበት በመሆኑ…

Read More →
ከስዊድን የመጡ በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች የአንገት በላይ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በየካቲት 12 ሆስፒታል እየሰጡ እንደሆነ ተገለጸ
By: Date: November 11, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

ከስዊድን የመጡ በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች የአንገት በላይ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እየሰጡ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ ከ300 በላይ የአንገት በላይ ቀዶ ሕክምና ፈላጊዎች ወረፋ እየጠበቁ እንደሚገኙም ታውቋል። በየዓመቱ ከስዊድን አገር የሚመጡ በጎ ፈቃደኛ ሐኪሞች በሆስፒታሉ ውስጥ ከአንገት በላይ ሕክምና ያለውን ተደራሽነት ለማስፋትም ትልቅ እገዛ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡ ከውጭ አገር የሚመጡ በጎ…

Read More →
ኦዴፓ የሚያስተዳድረው ክልል ባለሀብቶች በጋምቤላ መሬት እንዲያገኙ እየጣረ ነው፣ አዴፓም ተመሳሳይ ፍላጎት አለው
By: Date: November 11, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

ዋዜማ ራዲዮ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አዴፓ የሚመሯቸው ክልል ተወላጅ ባለሀብቶች በጋምቤላ ክልል ለጊዜው እየተሰራባቸው ያልሆኑ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ለመውሰድ በቅርቡ ሰፊ ጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች። ከ2003 አ.ም ጀምሮ የጋምቤላን ክልል ጨምሮ በአራት ክልሎች ለሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት ይሆናል ተብሎ ከሶስት ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በፌዴራል መንግስት ቋት ውስጥ ሲገባ…

Read More →
የግብፅ ከበባ እና ኢትዮጵያ
By: Date: November 6, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

ከ80 በመቶ በላይ ለዓለማችን ረጅሙ ወንዝ ናይል ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ ወንዟን በሚገባ እንዳትጠቀም ግብጽ ከመቶ ዓመታት በፊት አንስቶ የተለያዩ የማዳከሚያ ስልቶችን ስትጠቀም ቆይታለች። የማዳከሚያ ስልቶቹ በቀጥታ ጦር አዝምቶ ለመደብደብ ከመሞከር አንስቶ አስከ ረቂቅና ውስብስብ ሴራዎችን እስከመፈጸም ይደርሳል። ኢትዮጵያ ከስምንት ዓመት በፊት የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጀመሯን ተከትሎ ግብጽ በስውርና በግልጽ የተለያዩ ጫናዎችን በማሳረፍ ላይ ትግኛለች። ለአብነት…

Read More →
በቃሉ ወረዳ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ የመከላከል ሥራ ከባድ መሆኑ ተገለጸ፡፡
By: Date: November 5, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

በደቡብሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በሰብልና እንስሳት መኖ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ባልደረባችን አሊ ይመር ከቦታው የታዘበውን ገልጿል፡፡ የአካባቢው አርሶ አደሮች ተማሪዎች፣ የልዩ ኃይል አባላትና ሌሎችም በባሕላዊ መንገድ እያደረጉ ያለው የመከላከል ጥረት ብዙም ውጤት አለማምጣቱን ነው ያመለከተው፡፡ ‹‹አሁን ደክመናል፤ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተውጠን የሚሆነውን ሁሉ ቁጭ ብለን እያዬን ነው›› ብለዋል አርሶ አደሮቹ፡፡ የተቀናጀና…

Read More →
ፌዴራላዊ ስርዐቱ አወቃቀር የዜጎችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት አጋልጧል – የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን
By: Date: November 2, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፌዴራላዊ ስርዐቱ የተተገበረበት መንገድ ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ተጋላጭ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ተናገሩ:: ዶክተር ዳንኤል በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳብራሩት፤ ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋላጭ ያደረገው ፌዴራላዊ ስርዓቱ የተተገበረበት መንገድና የፌዴራል ስርዓቱ የመንግስት አወቃቀር አንዱ ችግር መሆኑን አሰረድተዋል:: የፖለቲካ ፓርቲ አወቃቀሩም ሌላው ምክንያት ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመው በተለየ ማንነት…

Read More →
በመንግሥት ጥሪ ሀገር ውስጥ ለገቡ ግለሰቦች የሚደረገው ጥበቃ ከማቋቋሚያ አዋጁ ውጭ ነው ተባለ
By: Date: October 31, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

በውጭ ሀገር ሆነው በተቃውሞ የራሳቸውን አቋም ሲያራምዱ የነበሩና በመንግሥት ጥሪ ሀገር ውስጥ ለገቡ ግለሰቦች ለደህንነታቸው ሲባል እየተደረገላቸው ያለው ልዩ ጥበቃ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ውጭ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ በአዋጁ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር ልዩ ጥበቃ የሚያደርግላቸው ሀገርንና ህዝብን ይጠቅማሉ ተብለው በመንግሥት ለተሾሙ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከውጭ ሀገር ለሚመጡ መሪዎች፣ የክብር እንግዶች መሆኑን አመልክቷል፡፡…

Read More →
በድሬደዋ ተፈናቃዮች የተጠለላችሁበትን ለቃችሁ ውጡ በሚል ቄሮ የሚባለው ቡድን ድብደባ ተፈጸመባቸው
By: Date: October 30, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

በድሬደዋ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚል ቄሮ የሚባለው ቡድን ድብደባ እንደፈጸመባቸው ተሰማ። ለኢትዮ 360 የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው 200 የሚጠጉት ተፈናቃዮች አካባቢውን ልቀቁ በሚል ድብደባ የተፈጸመባቸው ትላንት ከምሽቱ 4 ሰአት ጀምሮ ነው። በተለምዶ ዝንጀሮ ገደል በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩት ተፈናቃዮች አካባቢያቸውን እንዲለቁና በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ለመጠለል የተገደዱት በዚሁ የጥፋት…

Read More →
“አጥፊዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል” የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
By: Date: October 30, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

በተከሰተው ሁከት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ አካላት በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አሳሳበ። ኮሚሽኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እና ተሃድሶ እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች እንዳስገኘው ሁሉ ውስብስብ ተግዳሮቶችም እየገጠሙት ይገኛል ብሏል። በተለይም ከጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው ሁከት የተሞላ ነውጥ የበርካታ ሰዎች ሕይወት…

Read More →
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ነገ መግለጫ ይሰጣል
By: Date: October 30, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር

ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነገ ጥቅምት ሀያ ቀን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡ መግለጫው ከሰአት በኋላ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነገ ጥቅምት ሀያ ቀን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡ መግለጫው ከሰአት በኋላ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

Read More →
ኢትዮጵያ የሁለት መንግሥታት አገር
By: Date: October 30, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

በኃይሉ ሚዴቅሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ‹የውጭ አገር ፓስፖርት ይዛችሁ የምትበጠብጡን ሰዎች አገራችሁን ለቃችሁ ውጡ፤ አለያ ተውን›› የሚል ይዘት ያለው ንግግር ካሰሙ በኋላ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል የምትለዋን የአይጥ ተረት በመተረት ለመፋለም መዘጋጀቱን በገደምዳሜ ገለፀ፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ ምሽት ላይ በኤልቴቪ ቀርቦ ጠቅላይሚኒስትሩን፣ መንግሥታቸውንና ድርጅታቸውን በተደጋጋሚ ‹ውሸታም› እያለ ተቸ፡፡ ‹‹ይህንን የለውጥ ኃይል ደግፉት…

Read More →
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቀድሞ ተገንጥላሏል
By: Date: October 30, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር

ከአመት በፊት የህይወቴ አስቀያሚው የስራ ልምድ ብዬ የምሰይመው ስራ ውስጥ ተሳተፍኩ። ስራው መማሪያ መፅሃፍትና መምሪያ ማዘጋጀት ነበር ለኦሮሚያ ክልል ትት ቢሮ። የማስተበባር ስራ ነበር ድርሻዬ። በዚያውም አዘጋጆቸቹ የመጨረሻ የሚሉትን ረቂቅ ለህትመት ወደ ውጪ ከመላኬ በፊት የአርትኦት ስራ እሰራ ነበር። እጅግ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት ስራ ነበር። እኔ ስደርስ ከሌላ ፕሮጀክት ነበር ቡድኑን የተቀላቀልኩት የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ…

Read More →
በሰሞኑ ጥቃት ከ3 ሺ 366 በላይ ወገኖች ተፈናቅለዋል
By: Date: October 29, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር

ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች በተነሱ ግጭቶች ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ባሉበት ቦታ እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ። የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይረክተር አቶ ደበበ ዘውዴ እንደገለጹት፥ ባለፈው ሳምንት ተከስቶ በነበረው ግጭት ከምእራብ አርሲ ዶዶላ ተፈናቅለው በሁለት ቤተክርስቲያናት ለሚገኙ ዜጎች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች ተልኳል። በዶዶላ 3 ሺህ 366 ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን፥ እህል፣…

Read More →
ዝምታ ምንድነው? ስምምነት ወይስ ተቃውሞ?
By: Date: October 29, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

የአክቲቪስትና የሚዲያ ባለሀብት ጀዋር መሐመድ የተከበብኩኝ ጥሪ ተቀብለው ካለፈው ረቡዕ ዕለት ጀምሮ አደባባይ የወጡ ወጣቶች አመጽ ጋር ተያይዞ 67 ሰዎች መሞታቸውን እንደዋዛ ሰማን፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮምሽነር ከፍያለው ተፈራ ለሬውተርስ የዜና አገልግሎት ትላንት እንደተናገሩት ካለፈው ዕረቡ ዕለት ጀምሮ በተቀሰቀሰው አመጽ በድምሩ 67 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 49 ያህሉ በድንጋይ ተወግረው የሞቱ፣ 13 ቱ ደግሞ…

Read More →
ሥርዓት አልበኞች ለፍርድ ይቀርባሉ – የግሎባል አልያንስ መግለጫ
By: Date: October 29, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር,ማህበራዊ

በቅድሚያ ስሞኑን በኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ሃላፊነት በጎደለውና “እኛ የቄሮን ጉልበትና አቅም አሳይተናል ” እያለ የሚፈክረው አክትቪስት ነኝ ባዩ ባስተላለፈው ጥሪ ተነሳስተው አብዛኛውንና ስላማዊውን የኦሮሞ ወጣት የማይወክሉ ሥርአት አልበኞች በስላማዊ ዜጎች ላይ ባደረሱት ብሄርና ሃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ በአስቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡ ለቆስሉና ቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን በሙሉ ለደረስባቸው ጥቃት ዘግናኚና ኢስብአዊ ጥቃት የተስማንን…

Read More →
የባለጊዜዎቹ የመሬት ወረራ በጀሞ
By: Date: October 18, 2019 Categories: መንግስትና አስተዳደር Tags:

ወራሪዎቹ የተደራጁና ከጀርባቸው የሚደግፋቸው እንዳለ በሚገባ ያስታውቃሉ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለውጡን ተከትሎ እስካሁን በርካታ መሬቶች የተወረሩና ማንም ጠያቂ እንደሌለ እያየን ቆይተናል። ይሄው ይለይላችሁ ብለው ከአዲስ አበባ ከሶስት መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ድረስ በመኪና ተጭነው የመጡት ወራሪዎች ይዞታቸውን አረጋግጠው የተቀመጡ ይመስላል። ትናንት ምሽት በጀሞ አንድ ጀሞ ሁለት እና ጀሞ ሶስት ነዋሪዎች ምሽቱን በስጋት ያሳለፉ…

Read More →