Press "Enter" to skip to content

ባለቤታቸው ሠራተኛ በጥፊ በመምታቷ አምባሳደሩ ከኃላፊነት ተነሱ

የቤልጄሙ አምባሳደር ባለቤት አንድ ሠራተኛ በጥፊ በመምታቷ አምባሳደሩ ከኃላፊነታቸው ተነሱ። ፒተር ለስኮሂር በደቡብ ኮርያ የቤልጄም አምባሳደር ናቸው። ባለቤታቸው ዢንግ ዢኩ ስዑል ውስጥ አንድ ሠራተኛ በጥፊ ስትመታ ቪድዮ ተቀርጿል።

ሠራተኛዋ መደብር ውስጥ ትሰራ ነበር። የአምባሳደሩ ሚስት መደብር ውስጥ የተወችው ልብስ የሷ ይሁን ወይስ የተሰረቀ ስላልታወቀ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። የቤልጄም የውጪ ጉዳይ ሚንስትር እንዳለው የአምባሳደሩ ሚስት ኋላ ላይ የመደብሩን ሠራተኛ ይቅርታ ጠይቃለች። ሆኖም ግን አምባሳደሩ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መወሰኑን የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ሶፊ ዊልምስ ተናግረዋል። በአምባሳደርነት የቆዩት ለሦስት ዓመታት ነበር።

ኤምባሲው በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ “አምባሳደሩ እስካሁን በትጋት አገራቸውን አገልግለዋል። በቅርብ የተፈጠረው ነገር ግን ከዚህ በኋላ አብረውን እንዳይቀጥሉ አድርጓል” ብሏል።

ባለፈው ወር አምባሳደሩ “ለባለቤቴ ያልተገባ ባህሪ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለዋል። ባለቤታቸው ሠራተኛዋን በጥፊ ከመታች በኋላ ክስ እንዳይመሰረትባት የዲፕሎማት ጥበቃ መርህን ተጠቅማ ነበር። ሆኖም ግን ቤልጄም ጥበቃውን አንስታ የደቡብ ኮርያ ፖሊስ ጉዳዩን መመርመር ይችላል ብላለች።

ሠራተኛዋ በጥፊ የተመታችው ባለፈው ወር ነበር። የ63 ዓመቷ የአምባሳደሩ ሚስት ለአንድ ሰዓት ያህል ልብስ ሞክራ ከመደብር ስትወጣ፤ ለብሳ የወጣችው ልብስ የሷ መሆኑን ለማረጋገጥ ሠራተኞች ተከትለዋት ሄደዋል።

ሠራተኞቹ ልብሱ ከመደብሩ ሳይከፈል የተወሰደ ሊሆን ይችላል ብለው ነበር። የአምባሳደሩ ባለቤት አንዷን ሠራተኛ ወደ መደብሩ ስትከተል ለመከላከል የሞከረችን ሠራተኛ ገፍትራ በጥፊ መታለች። ይህም በደኅንነት መቆጣጠሪያ ካሜራ ተቀርጿል። የአምባሳደሩ ባለቤት ከዚህ ቀደም በስትሮክ ምክንያት ሆስፒታል ገብታ ነበር። መደብሩ ውስጥ ከተፈጠረው ውዝግብ በኋላ ፖሊስ ጥያቄ አቅርቦላታል።

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//chooxaur.com/4/4057774