ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ዜጎች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች ጎሐ ጽዮን ላይ የከፋ እንግልት እየደረሰባቸው ነው

ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ዜጎች እንዲሁም ተሽከርካሪዎች ጎሐ ጽዮን ላይ የከፋ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ቅሬታቸውን ለአሐዱ አሰሙ፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር ለመሄድም ሆነ ለመምጣት ጎሐ ጽዮን አካባቢ ያለው አለመረጋጋት ስጋት እንደሆነባቸው መግለጻቸውን ተከትሎ፤ አሐዱም በአካባቢው ምን እንደተከሰተ የአይን እማኞችን እና አሽከርካሪዎችን አነጋግሯል፡፡

በቦታው በአካል በመገኘት ምን እየደረሰ እንዳለ የታዘቡት የሚዲያ ባለሙያው አቶ አባይ ዘውዱ፤ ከአማራ ክልል የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን በማስቆምና ጉዳት በማድረስ በተለይም ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ክልከላ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ሌላኛው አሽከርካሪ በበኩላቸው ሚያዚያ 19/2013ዓ.ም ገብረ ጉራቻ ልዩ ስሙ አሊጎሮ አካባቢ በተሰነዘረ ጥቃት አንድ የመኪና ሾፌር እና የሰባት ዓመት ሕጻን ልጅ ሕይወታቸው እንዳለፈ ተናግረው የሕጻኗ አባትም የሕክምና እርዳታ እየተደረገለት እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

አሐዱ ጉዳዩን አስመልክቶ መረጃውን ለማጣራት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል መምርያ ኃላፊ ጋር ቢደውልም መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጋርም የተደረገው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ምላሽ አላገኘም፡፡ አሐዱ ራድዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//zuphaims.com/4/4057774