የታይም መጽሄት መቶ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ የተካተተው የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳራ መንክር ድርጂት

የ“ታይም” መጽሄት የአመቱ መቶ ተፅዕኖ ፈጣሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳራ መንክር ድርጅት የሆነው ግሮ ኢንተለጀንስ ተካተተ። ሳራ መንክር የ“ታይም” መጽሄት የፊት ሽፉን ገፅ ላይ ወጥታለች።

በኢትዮጵያ የተወለደችው ሳራ መንክር የዎል ስትሪት ኮሞዲቲ ሽያጭ ባለሙያ ነበረች፡፡ ይህንን ስራ በ2014 በመልቀቅ ኬንያ ውስጥ ግሮ ኢንተለጀንስ የተሰኘ ድርጅት አቋቋመች፡፡

ይህ ድርጅት የተመሰረተው ግብርናን በተመለከተ በመላው አለም ያለውን የመረጃ ክፍተት ለመሙላት በሚል ነበር፡፡ ድርጅቷም ባለፉት አመታት የምግብ ምርት ላይ ተፅእኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ከእህል ዘር እስከ አፈር ጥራትና አየር ንብረት ድረስ በርካታ መረጃዎችን አሰባስቧል፡፡

በመሆኑም ከተለያዩ ገበያዎች ባሰባቸባቸው በእነዚህ በትሪሊዮን የሚቆጠሩ መረጃዎች በመነሳት አሁን ድርጅቱ የአለምን የግብርና ምርት ፍላጎት፣ አቅርቦትና ዋጋ ለመተንበይ ችሏል፡፡

በግብርናና በከባቢ አየር ስጋት ዙሪያ በአለማችን በግንባር ቀደምትነት ከተቀመጡ መረጃ ተንታኝ ተቋማት መካከል የሳራ መንክር ግሮ ኢንተለጀንስ አንዱ ነው፡፡ የእሷ እቅድ ግን ከዚህም አልፎ ድርጅቱ አገራትና ምግብ አምራች ድርጅቶች የምግብ ሰንሰለታቸውን እንዲያስተካክሉ የሚያስችል ዘዴን መፍጠርና የአየር ለውጥ ፈተናን ለመቅረፍ እርዳታ ማድረግ ነው፡፡ ይህ እቅዷም የኢንቨስተሮችን ቀልብ ለመሳብ በቅቷል፡፡ ምንጭ መዝናኛ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//soaheeme.net/4/4057774