ኦሮሙማ ሰማዩንም ምድሩንም ኦሮሞ የማድረጊያ ፕሮጀክት እንጂ ኦሮሞነት ወይም የኦሮሞ ማንነት ማለት አይደለም

ኦሮሙማ ኦሮሞ ያልሆኑ ነገዶችን ኦሮሞ ማድረጊያ፣ የኢትዮጵያ ነገዶችን ጨፍልቆ በኦሮሞ ባሕልና ቋንቋ መሰልቀጥና መዋጥ፣ የኦሮሞ የተባለውን ሃይማኖት ብቻ እንዲቀበሉ ማስገደድና ባጠቃላይ ሰማዩንም ምድሩንም ኦሮሞ የማድረጊያ ፕሮጀክት እንጂ ኦሮሞነት ወይም የኦሮሞ ማንነት ማለት አይደለም። ይህንን የኦሮሙማ ትርጉም የሚነግረን የርዕዮተ ዓለሙ ፈጣሪ የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፈሰር አሰፋ ጃለታ ነው። በሌላ አነጋገር ኦሮሙማ ከኦሮሞ ማንነት ጋር አንድ አይደለም። እንዴውም ኦሮሙማ ለአብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ ጸረ ኦሮሞ የሆነ ፕሮጀክት ነው። በኦሮሙማ ፕሮጀክት እሳቤ መሰረት የክርስትና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነ ኦሮሞ እንደ ኦሮሞ አይቆጠርም።

የኦሮሙማ ፕሮጀክት አይዲዮሎጉ ፕሮፈሰር አሰፋ ጃለታ አንድ ኦሮሞ የክርስትናና የእስልምና እምነትን ከዋቄ ፈታ እምነት የሚመርጥ ከሆነ በፍቃዱ ኦሮሞነቱን እንደተወ ይቆጠራል ይላል። በኦሮሙማ እሳቤ አንድ ሰው ኦሮሞ የሚሆነው የዋቄፈታ እምነት ተከታይ ሲሆን ብቻ ነው። ስለዚህ ኦሮሞማ የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን የኦሮሞ ተወላጅ ጭምር ማጥፊያ ፕሮጀክት ነው።ኦሮሙማ ይኼው ነው። ከዚህ ውጭ ኦሮሙማ ሌላ ትርጉም የለውም። አቻምየለህ ታምሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//chooxaur.com/4/4057774