ኬንያዊያን የዓለም ገንዘብ ድርጅት ለአገራቸው ብድር እንዳይሰጥ ጠየቁ

በወል የንቅናቄ ሐረግ ኬንያን ማበደር አቁሙ የሚል ዘመቻ የከፈቱ ሲሆን ፊርማ በሚሰበስቡበት ድረ ገጽም ለምን ኬንያ ተጨማሪ ብድር ሊሰጣት እንደማይገባ ይዘረዝራሉ።ይህ ዘመቻ የተጀመረው የዓለም ገንዘብ ድርጅት ለኬንያ 2ቢሊዮን ተኩል ዶላር ለኬንያ ከኮቪድ መነቃቂያ ብድር መፍቀዱት ተከትሎ ነው።

የአገሪቱ ዴይሊ ኔሽን እንደጻፈው የኬንያ አገራዊ ብድር መጠን ባለፈው ዓመት ብቻ 1 ትሪሊዮን ሺሊንግ አልፏል። ለአገሬ አታበድሩ ዘመቻ አቀንቃኞች የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያ ከዚህ ቀደም «አገሬ በቀን 2 ቢሊዮን ሺሊንግ በሙስና ታጣለች»ማለታቸውን እንደ ማስረጃ አቅርበዋል። የኬንያ ግምጃ ቤት ዋና ጸሐፊ ኡኩር ያታኒ ብድሩ ለኬንያ ምጣኔ ሀብት ማነቃቂያ እጅግ አስፈላጊ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።ለአራችን ብድር አትስጡ የሚለው ንቅንቄ ከፊርማ ዘመቻ ባሻገር በዓለም ገንዘብ ድርጅት ማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ ጭምር በመሄድ ነው ድርጅቱ ብድር ከመስጠብ ይቆጠብ እያሉ ያሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *