ኢትዮጵያ ቡና የኤርትራን ብሄራዊ ቡድን አምበል አስፈረመ

ኢትዮጵያ ቡና ኤርትራዊውን ሮቤል ተክለሚካኤልና ናትናኤል በርሔን አስፈረመ። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል። ኢትዮጵያ ቡና የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን አንበል እና የቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የነበረው እና የሴካፋ ሀገራት ውድድር ላይ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠውን ሮቤል ተክለሚካኤል ማስፈሙን ነው የገለፀው።

በተጨማሪም ለደደቢት እንዲሁም ለከፋ ቡና የተጫወተውን ናትናኤል በርሔን እንዳስፈረመ በክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ገልጿል። ሁለቱ ተጫዋቾች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያቆያቸውን ስምምነት ከክለቡ ጋር ተፈራርመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *