Press "Enter" to skip to content

የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አወቃቀሯ ነው – ሙሀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

በመጪው ግንቦት 2012 ዓ.ም. በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ ከተመዘገቡ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪ፣ ከ120 በላይ ግለሰቦች በግል ለመወዳደር ዕጩ ሆነው መቅረባቸው ተሰምቷል፡፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት በግል ለመወዳደር ዕጩ ሆነው ከቀረቡት መካካል መምህር፣ ደራሲ፣ የማኅበረሰብ አንቂና አሁን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አማካሪ ሙሀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይገኝበታል፡፡ ዲያቆን ዳንኤል በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ምርጫ ወረዳ 28 ‹‹ኢትዮጵያዊነት በርቱዓዊነት›› በሚል መሪ ቃል ለውድድር ቀርቧል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአማካሪነት ሥራው በተጨማሪ ፓርላማ ለመግባት ምን እንዳነሳሳው? ቢገባ ምን ዓይነት የተለዩ ሐሳቦችን ይዞ እንደሚመጣ? ስለአገራዊ አጠቃላይ ሁኔታዎችና ፈተናዎች፣ በመጪው ምርጫ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ተስፋና ሥጋቶች፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ሲሳይ ሳህሉ ከሙሀዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ተጠናቅሯል፡፡

ሪፖርተር:- ከአማካሪነት ሥራህ በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግሮች (Speeches) ይጽፋል ትባላለህ፡፡ በተጨማሪም እንደ ልዩ አማካሪ ነውም የሚሉህ አሉ፡፡ እስኪ ስለዚህ ጉዳይ ንገረን፡፡

ዲያቆን ዳንኤል:- በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት ነው የማገለግለው፣ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ ነኝ፡፡ በተለይ በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች የተሻሉ እንዲሆኑ ሐሳብ እሰጣለሁ። በሐሳብም፣ ፕሮግራሞቹ የተሳኩ እንዲሆኑም ዕቅዶች በሚኖሩበት ጊዜ ሁለገብ አገልግሎት እሰጣለሁ።

ሪፖርተር:- ቋሚ ሥራህ ነው ማለት ነው?

ዲያቆን ዳንኤል:– አዎ!እንደቋሚሥራነውየምሠራው፡፡

ሪፖርተር:- የብዙ አገሮች መሪዎች ንግግር ጸሐፊ አላቸው፡፡ በተለይ ከአንተ የሥነ ጽሑፍ ሰው መሆን ጋር በተገናኘ ይመስላል የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሥነ ጽሑፋዊ ይዘት በማየት፣ ንግግሩን የሚጽፈው ዳንኤል ክብረት ነው የሚባለው ጉዳይ በተደጋጋሚ ይነሳል። እውነት ነው እንዴ?

ዲያቆን ዳንኤል:- እንግዲህ አንደኛ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያላቸው እውቀት ሰፋ ያለ ነው፡፡ እኔ እስከማውቀው በሥነ ጽሑፍም እንዲሁ ነው፡፡ የአብዛኞቹን ደራሲያን መጽሐፍት አንብበዋል፡፡ በቅርብ እስከወጣው የበድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) መጽሐፍ ድረስ ያነባሉ። ከዚያ በተጨማሪ ለኪነ ጥበብ የተለየ ፍላጎት አላቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ቋንቋዎችን ያውቃሉ። ብዙ ቋንቋና ብዙ ባህል ስታውቅ ብዙ ነገር ለመግለጽ አትቸገርም። ከዚያ የተረፈውን ጉዳይ ሌሎቻችን እንደ ድርሻችን የምናሟላው ይኖራል፡፡ ነገር ግን መነሻውና ትልቁ ድርሻ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው።

ሪፖርተር፡– በቀደሙት ዘመናት ለኢትዮጵያ ነገሥታት የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ከጎናቸው በመሆን እንደ አማካሪነት ያገለግሉ ነበር፡፡ የአንተ ወደ ቤተ መንግሥት መግባት የዚህ ዓይነት አንድምታ ይኖረው ይሆን?

ዲያቆን ዳንኤል፡– የእኔ ወደዚህ መምጣት የቤተ ክርስቲያን ሰው የመሆንና ያለ መሆን ጉዳይ ሳይሆን፣ እኔ ምናልባት በእሳቸው ጉዞ ውስጥ ላበረክተው ከምችለው አስተዋጽኦ አንፃር ነው እዚህ ቦታ ያለሁት፡፡ የትም ቦታ ብሄድ ሃይማኖተኝነቴ አብሮኝ ይሄዳል፡፡ እሱ የተፈጠርኩበት፣ የተመሠረትኩበት፣ የተሠራሁበትና እኔነቴን የፈጠርኩበት ስለሆነ ነው፡፡ እሳቸውም ደግሞ ሃይማኖተኝነታቸው አብሯቸው ይሄዳል፡፡ የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚከተሉ ሰዎችም እንደዚያው ማለት ነው፡፡ አንድ ያደረገን፣ የሚያግባባንና የሚያሠራን ኢትዮጵያዊነታችን ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ያለን ራዕይና ተስፋ ተመሳሳይ ነው፡፡ እናም እሱ ነው አብሮን እያሠራን ያለው፡፡ ምናልባት እኔ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጉዳዮች ስለምታወቅና ሌሎች ሰዎች በሙያቸው ብቻ ስለሚኖሩ፣ ሰው የሚያውቀው ላይ ብቻ ዓይኑን ስለሚተክል ካልሆነ በስተቀር ከእኔ በላይ አስተዋጽኦ ያደረጉ፣ ከእኔ በላይ የሚሠሩና ከእኔ በላይ የሚደክሙ ሰዎች አሉ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን የመታየት ዕድል የላቸውም፡፡ እኔ በየመድረኩ ሰው ስለሚያውቀኝና እዚያ ሲያየኝ ጎልቶ የመታየት ሁኔታ በመኖሩ ነው፡፡

ሪፖርተር፡– ምን ዓይነት ጉዳዮችን ነው የምታማክረው?

ዲያቆን ዳንኤል፡– ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ነው በብዛት የማተኩረው፡፡ የጤና፣ የትምህርት፣ የውኃና የመሳሳሉትን አይደሉም፡፡ ለእነዚህ ማኅበራዊ ጉዳዮች ራሱን የቻለ ትልቅ አማካሪ አላቸው፡፡ ለእኔ ግን ብዙ ጊዜ በእነሱ መዋቅር ውስጥ የማይገኙ በርካታ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ጉዳዮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የተለየ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ጉዳይ፣ የኢትዮጵያ የታሪክ፣ የባህልና የቅርስ ጉዳዮች፣ ለተለያዩ አካላት ሊደረጉ የሚገቡ ጉዳዮች ለምሳሌ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለሴቶች፣ ለቅርስ ወይም መሰል ቦታዎች የሚደረጉ የተለያዩ ዝግጅቶች አሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ፡፡ እነዚህ ዝግጅቶች ኢትዮጵያዊ መልክና እሴት እንዲኖራቸው ከማድረግ በተጨማሪ፣ የሚሠሩ ሙዚየሞችና የሕዝብ መናፈሻ ቦታዎች አሉ፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የሚከናወኑ በርካታ ነገሮችን ከታሪክ፣ ከባህልና ከኢትዮጵያዊ እሴት ጋር ከማድረግ አኳያ ነው ዋነኛው ሥራዬ፡፡

ሪፖርተር፡– በግንቦት 2013 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ በግል ዕጩ ሆነህ ቀርበሃል፡፡ ወደ ፖለቲካ ለመግባት ምን አነሳሳህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡–ከምርጫበኋላያሉትዓመታትበኢትዮጵያለዴሞክራሲናለፖለቲካጉዞበጣምመሠረታዊናቸውብዬአምናለሁ፡፡እርግጠኛነኝወይምተስፋአደርጋለሁየሕገመንግሥትናየፖሊሲዎችማሻሻያይኖራል፡፡በተጨማሪምበአወቃቀሮች፣በአስተሳሰቦችና በበርካታነገሮችላይማሻሻያዎችይኖራሉብዬእገምታለሁ፡፡ምክንያቱም የዓብይአህመድ (ዶ/ር) መንግሥትመጀመርያበፓርቲውበኩልተዋቀረ፡፡ከዚያፓርቲውሲለወጥየእኛአገርየጠቅላይሚኒስትርአመራረጥከፓርቲማሸነፍጋርስለሚሄድ፣ይህለውጥደግሞ በመንግሥትላይለውጥአመጣ፡፡ይህመንግሥትደግሞወደሕዝብቀርቦሕዝባዊድምፅየማግኘትዕድልአልነበረውም፡፡በመሆኑምበምርጫድምፅከተሰጠበኋላአብዛኞቹየኢትዮጵያየፖለቲካፓርቲዎችእርግጠኛነኝበአንድምበሌላየማነስወይምየመብዛትካልሆነበስተቀር፣የሚወከሉበትአዲስዓይነትፓርላማይኖራልብዬአስባለሁ፡፡እሱብቻሳይሆንፓርቲዎችያቀረቧቸውዕጩዎችሲታዩ፣ነገሩንየዋዛአድርገውእንዳልወሰዱትታየለህ፡፡ራሱገዥውፓርቲንጨምሮኮሮጆእንደዚህአድርጌአሸንፋለሁየሚልአካሄድውስጥእንዳልገባታያለህ፡፡እንደዚያቢሆንኖሮዝምብለህእንዲያው ‹‹ከዝንጀሮቆንጆምንይመራርጧል››ብለህማስቀመጥትችልነበር፡፡ነገርግንወደእሱአልገባም፡፡በጣምከባድሚዛንየሆኑሰዎችንበማዘጋጀትለምርጫውበጣምትኩረትሰጥቶታልማለትነው፡፡

ሌሎች ፓርቲዎችም ሲታዩ በጣም ትኩረት ሰጥተውታል፡፡ ስለዚህ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉዞ በጣም መሠረታዊ ለውጦች የሚታዩበት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ እንዲህ ባለው ጉዞ ውስጥ ደግሞ ቀደም ሲል የነገርኩህ የኢትዮጵያዊ እሴቶች ባህሪ፣ ማንነት፣ የሕዝቦች ግንኙነትና አንጡራ ሀብት ቦታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የእኛ አገር ሕገ መንግሥትም በለው ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ሕግጋት የተመጣጠነ የአገር ባህል እጥረት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን የሚገፋ ሰው ያስፈልጋል ብዬ ገመትኩ፡፡ እናም ለእነዚህ እሴቶች ድምፅ የሚሆን አካል ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜ ፓርቲዎች እንዲህ ዓይነት ነገር ለመውሰድ የርዕዮተ ዓለም ቅጅ ስለሚሆን በጣም ይቸግራቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት እሴቶችንከፓርቲወጣብሎየሚገፋ ያስፈልጋል፡፡ወደፓርቲዎችም፣ወደሕጎችም፣ወደሁሉምአቅጣጫዎችነውእኔለመግፋትየማስበው፡፡ወደገዥውፓርቲምበለውወደተፎካካሪፓርቲዎችም፣ወደሕጎችም፣ወደአሠራሮችምየሚገፋአካልያስፈልጋልብዬስላመንኩነውቢያንስበሚቀጥሉትአምስትዓመታትማገልገልአለብኝብዬየተነሳሁት፡፡

ሪፖርተር፡– ምናልባት ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባልነት ስትሰየም በፓርላማው በቀረበበት ተቃውሞ ምክንያት በቁጭት ነው ወደ ፖለቲካው የመጣው የሚሉ አሉ፡፡ የሚባለው እውነት ይሆን እንዴ?

ዲያቆን ዳንኤል፡– እኔ ይገርምሃል እሱን ጉዳይ ሰዎች ሲያነሱት ነው ትዝ የሚለኝ እንጂ፣ ሰው ሠራሽ ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ያን ነገር ዝም ብለህ ስታስበው ‹‹የዋጋ ግሽበት›› የገጠመው የፓርላማ ውሎ ነው፡፡ ማውጣት ካለበት ዋጋ ይበልጥ የጋሸበ ዋጋ ነው ያወጣው፡፡ አንደኛ የኢትዮጵያ ፕሬስ ቦርድ ነው ጉዳዩ፡፡ እሱን ትተህ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ቦርድ ቢሆን ኖሮ ትንሽ ቢያከራክር አይገርመኝም ነበር፡፡ ወይም ለአገሪቱ ጠቅላላ ፕሬስ ተቆጣጠሪ አካል ወይም መመርያ የሚያወጣ፣ ወይም ለሚኒስትርነት ቢሆን እሺ ይሁን፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ አባልነት ያን ያህል የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለዚህ ፓርላማው የዋጋ ግሽበት ገጥሞት ነበር የዚያን ቀን፡፡ ሌሎች ነገሮች ናቸው ጉዳዩን ወደዚያ ያመጡት፡፡ ሁለተኛ ደግሞ እኔ ቀድሞ ከዓመት በፊት የቦርድ አባል ሆኛለሁ፡፡ ተመልሶ ለድምፅ መቅረብም አልነበረብኝም፣ የአሠራርም ግድፈት ነበረበት ሒደቱ ራሱ፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ሁለት ጊዜ ድምፅ አይሰጥበትም፡፡ ስለዚህ እሱን ከቁምነገር አልቆጠርኩትም፡፡ እንዳልኩህ የእኔ መነሻ የዚያ ቁጭት ሳይሆን ሒደቱን ማገዝ አለብኝ፡፡ ሁልጊዜ ለምንድነው ሌሎች ሰዎችን የምንወቅሰው? ወይም ‹‹ከበሮ በሰው እጅ ሲያዝ ያምር…›› እንደሚባለው ለምን የሚይዙትን እንወቅሳለን? ለምን እኛስ ከሚይዙት ወገን አንሆንም? ከሚወቀሱት ወገን ለምን አንሆንም? የሚል ሐሳብ ይዤ ነው የገባሁት፡፡

ሪፖርተር፡– አንድ ሰው ወደ ፖለቲካ ሲመጣ የራሱ የሆነ አቋም ይዞ ነው፡፡ አንተ ደግሞ የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥትን ነው የምታማክረው፡፡ ይህ መንግሥት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የሚመራ ነው፡፡ ተፎካካሪ ሆነህ ስትቀርብ ጉዳዩ የሚያጋጭ አይሆንም ወይ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- በእኔ ላይ ተፅዕኖ አያሳድርብኝም፡፡ ቅድም እንዳልኩህ የእኔ ሐሳብ እነዚያ ያልኳቸውን ጉዳዮች መግፋት ነው፡፡ እንዲገፉ ከምፈልጋቸው ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ብልፅግና ፓርቲ ነው፣ ሌሎች ፓርቲዎችም ጭምር፡፡ እኔ አሁንም እኮ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር እሠራለሁ፡፡ ከተለያዩ አካላት ጋር እሠራለሁ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊነታቸውን ያደረጁ፣ ለኢትዮጵያ እሴቶች የቆሙ፣ ለኢትዮጵያ ምንጊዜም የማይደራደሩ ተቋማትን ማየት ነው ፍላጎቴ፡፡ ፓርቲዎች የሲቪክ ማኅበራት፣ የሃይማኖት ተቋማትና የሙያ ማኅራት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነሱ ውስጥ የኢትዮጵያ እሴቶች ገብተው ማየት ነው የእኔ ዓላማ፡፡ ያን ያህል ከፓርቲዎቹ ጋራ በርዕዮተ ዓለም የሚያከራክረኝ ወይም የሚያጨቃጭቀኝ ጉዳይ የለም፡፡ ብልፅግናም ሆነ ሌሎች ፓርቲዎች እዚያ ቦታ ይምጡ፡፡ እነዚህን ነገሮች የሚቀበሉ እስከሆነ ድረስ፡፡ እስካሁን እንዳየሁት ደግሞ ብልፅግና ፓርቲ ይህንን ጉዳይ አልቀበልም ብሎ አያውቅም፡፡ እኔ እንግዲህ ብልፅግና፣ ብልፅግና ሆኖ መሥራት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ አብሬው ሠርቻለሁ፡፡ እኔ አባል ሳልሆን ብዙ አባላት ባሉበት እስካሁን ባየሁት ሒደት የተሻለ ሐሳብ አምጥቼ፣ ሞግቼ፣ የተሻለ ነገር ሰጥቻቸውና ተከራክሬያቸው አንቀበልም ያሉት ጉዳይ የለም፡፡

ሪፖርተር፡– ስለዚህ ብልፅግና እያደረገ ያለውን ትደግፋለህ ማለት ነው?

ዲያቆን ዳንኤል፡- ለእኔ ትልቁ እንዲያውም ለኢትዮጵያ ትልቁ ለውጥ እኮ ኢሕአዴግ ወደ ብልፅግና የመጣበት ወቅት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትን ለመያዝ የሚያደርገው ጥረት ነው፡፡ ፈተናዎችም እነሱ ናቸው፡፡ ትልቁ ፍትጊያም እሱ ላይ ነው፡፡ ወደ እሱ በሚመጣው ሐሳብና ከእሱ ለመውጣት በማይፈልጉ አሮጌ ሐሳብ መካከል ነው ትግሉ፡፡ ይህንን ትግል ደግሞ ሁላችንም ማገዝ ነው ያለብን፣ ለኢትዮጵያ ስለሚጠቅም፡፡ ትልቁን ዝሆን ጥለህ ድመቶችንና ሌሎችን ይዘህ የትም ልትደርስ የምትችልበት ዕድል እኮ የለህም፡፡ ዝሆኑ ሲስተካከል ግን ሁሉም ነገሮች ይስተካከላሉ፡፡

ሪፖርተር፡– አንተና አንድ የብልፅግና ተወካይ በምትወዳደሩበት አካባቢ መራጮች ሁለታችሁን እንዴት ለይተው መምረጥ ይችላሉ? አንተ ከብልፅግና በተሻለ ምን ዓይነት አማራጭ አመጣሁላችሁ ትላቸዋለህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- እኔ እንዳልኩህ ነው፡፡ ከብልፅግና የተሻለ የተለየ ነገር አለው ብሎ አይደለም የሚመርጠኝ፡፡ በብልፅግና ላይ የተለየ ነገር ያመጣል ብሎ እንጂ የሚመርጠኝ፡፡ በጊዜው፣ ወይም በሌሎች ፓርቲዎች፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተለየ ነገር ይጨምርልናል ብሎ ነው እኔን የሚመርጠኝ እንጂ እነሱን ያሸንፍልናል ብሎ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እኔ ፓርቲ ወይም ድርጅት አይደለሁም፡፡ ግን አንተ በትልቅ ድስት በተሠራ ወጥ ላይ አንድ ጭልፋ ቅቤ የምታደርገው ወጡን ከክክ ወጥነት ወደ ምስር፣ ወይም ከዶሮ ወጥነት ወደ ክትፎነት ለመቀየር አይደለም፡፡ የወጡን ጣዕም ግን ይቀይረዋል፡፡ የእኔ ሚናም እንዲህ ነው፡፡

ሪፖርተር፡– አንዳቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምን አልተቀላቀልክም? ከፓርቲዎች ጥያቄ አልቀረበልህም? ወይስ አንተ ምታራምደውን ሐሳብ የሚቀርብ ያላቸው አጣህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- እኔ ከድሮ ጀምሮ በፓርቲ ውስጥ መታቀፍ አልመኝም፡፡ ነገር ግን ጥያቄ ቀርቦልኛል፡፡ እኔ ፓርቲ ውስጥ ለመግባት እቸገራለሁ፡፡ ሐሳቦች ከፓርቲ ይሰፋሉ ብዬ ነው የማስበው፡፡ ስለዚህ ለእነሱም ምቹ አይደለም፡፡ ለእኔም ምቹ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ የሚሄዱትን ተቋማት በሙሉ ግን ማገዝ እችላለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ኢዜማ የተመሠረተ ጊዜ የምሥረታ ጉባዔውን የኢትዮጵያ የስብሰባ ማዕከል ሲያደርግ ከተናጋሪዎቹ አንዱ እኔ ነበርኩ፡፡ ኢዜማ በተመሠረበት ጊዜ ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ፣ ገዥውን የሚገዳደሩ፣ የሚያርሙ፣ ስህተቱን እንዲያርም አርዓያ የሚሆኑ ፓርቲዎች ያስፈልጉናል ብዬ ተናግሬያለሁ፡፡ እንዲህ ያልኩት ግን የኢዜማ ፓርቲ አባል ስለሆንኩ አይደለም፣ ለኢትዮጵያ ስለሚጠቅም እንጂ፡፡

ሪፖርተር፡– ዲያቆን ዳንኤል በምርጫው አሸንፎ ወደ ፓርላማ ቢገባ እንደ አንድ ተወካይ የሕዝብ ድምፅ ማሰማት እንጂ፣ ካለው የፓርላሜንታዊ ሥርዓት አኳያ ወደ መሪነት ሊያበቃ የሚችል ዕድል የለውም፡፡ ምናልባት ከተመረጥክ በኋላ ፓርላማ ውስጥ ሆኖ ድምፅ መስጠት ብቻ ለመረጠህ ሕዝብ በቂ ነው ብለህ ታስባለህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- እንግዲህእሱእንደሒደቱነውየሚወሰነው፡፡ለምሳሌቅድምያልኩህፖሊሲዎችናስትራቴጂዎችይመጣሉ፡፡በእኛአገርየፓርላሜንታዊሥርዓትውስጥወደፓርላማውበሚገቡስድስትወይምሰባትፓርቲዎች መካከልፍትጊያበሚኖርበት፣ኮሚቴዎችበሚቋቋሙበት፣የተለያዩሒደቶችበሚኖሩበትጊዜማነውእንዲህዓይነትፓርቲዎችንሊያቀራርብየሚችለውያልክእንደሆነእንደእኔዓይነትሰውነው፡፡የዚህምየዚያምፓርቲአባልያልሆነ፡፡ ነገርግንሁለትፓርቲዎችተቀራርበውለኢትዮጵያእንዲሠሩየሚያደርጉሰዎችያስፈልጉናልባይነኝእኔ፡፡ሁሉምበፓርቲየታጠረበሚሆንበትጊዜሁሉምየየራሱአለው፣በየራሱድርጅትውስጥተነጋግሮነውየሚመጣው፡፡እንዲህበሚሆንበትጊዜከዚህዓይነትውሳኔመውጣትሲያቅታቸው ማነው ሁለቱንየሚያቀራርባቸው?ወይምየተቋጠረውንቋጠሮየሚፈታ?ስትልከውጭልታመጣአትችልም፣ምክንያቱምየፓርላማሥራስለሆነ፡፡እንዲህ ያለ ጉዳይ ሲያጋጥም እንደእኔዓይነትሰውነውበእነዚህፓርቲዎችመካከልየተቀራረበናለኢትዮጵያየሚጠቅም ሐሳብ ላይ የሚያደርሳቸው፡፡ስለዚህለእኔመሪነትእሱነውእንጂ፣ሊቀመንበርወይምሚኒስትርመሆንንአይደለምመሪነትየምለው፡፡ትልቁመሪነትየሐሳብመሪነትነው፡፡

ሪፖርተር፡– በግንቦቱ ምርጫ ለመሳተፍ 125 የግል ተወዳዳሪዎች ቀርበዋል፡፡ የሃይማኖት አስተማሪዎችና ለእምነት ቅርብ የሆኑ ግለሰቦች ተስተውለዋል፡፡ በግል ተወዳዳሪነት የመቅረብና የእምነት ሰዎች በብዛት ወደ ፖለቲካው መግባት ምንን ሊያመላክት ይችላል?

ዲያቆን ዳንኤል፡- አሁን የእምነት ሰዎች እየተመለሱነው፡፡በኢትዮጵያታሪክእኮእንዲያነውየነበረው፡፡የእምነትሰዎችነበሩየፓርላማአባላት፡፡በአፄኃይለሥላሴፓርላማ ትልልቆቹሰዎችናመሪጌቶችነበሩየፓርላማአባላት፡፡ከዚያግንጠፉ፡፡ደርግምበተወሰነመጠንሸንጎለማምጣትሲፈልግአምጥቶታልእኮ፡፡ለምሳሌእነአቡነተክለ ሃይማኖትየሸንጎአባልነበሩ፡፡በኋላምእነአቡነመርቆሪዎስየሸንጎአባልእንዲሆኑአድርጓል፡፡የእስልምናናየፕሮቴስታንትመሪዎችየሸንጎአባልሆነውበአገሪቱጉዳችላይየራሳቸውንሐሳብእንዲገልጹአድርጓል፡፡ይህእኮትክክለኛአካሄድነው፡፡እኔእንዲያውምየኢትየጵያፓርላማየርዕዮተዓለምብቻሳይሆን፣የሃይማኖትአተያየቶችናባህላዊእምነቶችእዚያውስጥቦታሊኖራቸውይገባል እላለሁ፡፡ቢቻልወደፊትየተረሱአካባቢዎችበደንብመታየትይኖርባቸዋል፡፡አካልጉዳተኞችየግድመወከልአለባቸው፡፡አካልጉዳተኞችንየግድአሸንፉልትልስለማትችል፣ተሰብስበውቢያንስእነሱብቻወኪላቸውንየሚመርጡበትአሠራርመምጣትአለበት፡፡ካልሆነግንየማይወከሉሐሳቦችይኖራሉ፡፡ለምሳሌአንዳንድብሔረሰቦች 3,000 ወይም 4,000 ሰዎች ይዘውነገርግንተደማምረውነውየሚመጡት፡፡ስለዚህእነሱየሚወከሉበትንመንገድመፈለግአለብን፡፡ሁሉንምነገርበአንድቅርጫትማምጣትየለብንም፡፡ሁሉንምነገር አንድአድርገንየምናይበትየዴሞክራሲአካሄድብቻአያስኬድም፡፡አንድ ዓይነትዴሞክራሲለሁሉምዓይነትበሽታእንዴትመድኃኒትሊሆንይችላል?ለተለያዩበሽታዎችየተለያዩመድኃኒቶችነውይዘንመምጣትያለብን፡፡እናምእንዲህዓይነትየአወካከልሥርዓቶችመምጣትአለባቸውብዬነውየማስበው፡፡ ፓርላማውየፓርቲዎችብቻለምንይሆናል?ምክንያቱምፓርቲዎችብቻአይደሉምይህችንአገርየሚመሯት፡፡ሌሎችምይመሯታልእኮ፡፡እንዲያውምወደፊትእንዲህዓይነትነገሮችየሚወጡበትአሠራርመፈጠርአለበት፡፡

ሪፖርተር፡– ቀጣዩ ምርጫ ለኢትዮጵያ ምን ዓይነት ተስፋ ይዞ ይመጣል ብለህ ታስባለህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- አሁን ብዙ ሰዎች ቀጣዩ ምርጫ ላይ ሥጋት አለን ይላሉ፡፡ እኔ የፓርቲዎችን አካሄድ ሳየው የመጣጣም እንጂ፣ የመፈራረስ ወይም ጨዋታ ፈረሰ ዓይነት ሳይሆን የተሻለ ጨዋነት እያየሁ ነው፡፡ የተረጋጋ አካሄድ አያለሁ፡፡ አንዱ አንዱን በጠረባ ጥዬው ልለፍ ዓይነት አሁን አላይም፡፡ አብዛኞቹ በምርጫ የተነሱ ሐሳቦች ይነስም ይብዛም ውክልና የሚያገኙ ይመስለኛል፡፡ እናም ፓርቲዎቹ ያቀረቧቸው ሰዎች በፓርቲ ብቻ ይገደባሉ ብዬ ለመገመት ይከብደኛል፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች ከፓርቲ ይሰፋሉ፡፡ በጣም የገረመኝ ነገር ከዚህ በፊት እኛ አገር የነበረው የፓርቲ አባልነት እንጀራ እየሆነ ነበር የተቸገርነው፡፡ በተጨማሪም የፓርቲ አባልነት መሬት፣ መኪና፣ የውጭ ትምህርት ዕድል፣ አበል፣ ኮፍያና ቲሸርት፣ የቤት ኪራይ ነው፡፡ አሁን የፓርቲ አባልነታቸው ኮፍያና ቲሸርት የማይሆንላቸው፣ እንዲሁም ኮፍያና ቲሸርት አሰፍተው ለፓርቲያቸው ሊሰጡ የሚችሉ፣ በፓርቲ አባልነት መኪና የማይወስዱ፣ እንዲያውም መኪና ሊሰጡ የሚችሉ፣ ውጭ አገር በፓርቲ አባልነት የማይሄዱ፣ ውጭ አገር መሄድ የሰለቻቸው ሰዎች እየመጡ ነው፡፡ ይህ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ክርክሩ በፓርቲዎች መካከል እንዳይመስልህ፣ በአንድ ፓርቲ ውስጥ ፉክክር አለ፡፡ ይኼ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሕይወት ነው፡፡ አንድ ባህር እኮ ሌላ ባህር ሲጨመርበት አይደለም ሕይወት የሚያገኘው፡፡ እንዲያውም እዚያው ባህር ውስጥ ንፋስ እየመጣ ባህሩን ሲያገላብጠው ሕይወት ይኖረዋል፡፡ አሁን እንዲህ ዓይነት ነገር እጠብቃለሁ፡፡

ሪፖርተር፡– በኢኮኖሚ ከበድ ያሉና ራሳቸውን የቻሉ ሰዎች እየመጡ ነው ማለትህ ነው?

ዲያቆን ዳንኤል፡– አዎ! ቤትና መኪና ያላቸው፣ ተምረው የመጡ ሰዎች ሲገቡ በጣም ትልቅ ነገር ነው፡፡ አሁንም ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ብዙ ክፍት የመንግሥት ቤት የምናገኝ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ቤትና መኪና ያላቸው ናቸው፡፡ መንግሥታዊ ቤት አቅራቢ ድርጅት ትንሽ ዕረፍት የሚያገኝ ይመስለኛል፡፡

ሪፖርተር፡– አንተ ወደ ሥነ ጽሑፍ የምታደላ፣ ብዙ ጊዜ የምታውቀውም በቋንቋና እንዳልከውም በባህል ረገድ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ወደ ምርጫ እየመጡ ያሉ ፓርቲዎችም ሆነ አንተ፣ ለኢትዮጵያ ብንተገብረው ይበጃል የምትሉት የኢኮኖሚ ርዕዮተ ዓለም ምንድነው?

ዲያቆን ዳንኤል፡- ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ቁጭ ብሎ በመመካከርና ባለሙያዎቹን በማዳመጥ፣ ኢትዮጵያዊ መፍትሔ ማምጣት ነው ትልቁ ጉዳይ፡፡ ለኢትዮጵያ ከታይላንድ ወይም ከቻይና ወይም ከሌላ አውሮፓ አገር እናመጣና መከራ እናያለን፡፡ ሶማሌ ተራ የሚሠራውን ዓይነት እንኳ ሞደፊክ ሳንሠራው ነው ትልቅ አደጋ እየመጣ ያለው፡፡ ቁጭ ብለን እስኪ እንነጋር፡፡ ብቁ ባለሙያዎች አሉን፡፡ ፓርላማውና ፓርቲዎች ለእነዚህ ሰዎች ዕድል መስጠት አለባቸው፡፡ የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያዊ መፍትሔ አምጡ ማለት አለበት ፓርላማው፡፡ ጃፓን የቀናችው እኮ የጃፓን ንጉሥ ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ባደረገው ነው፡፡ የጃፓንን ችግር የሚፈታ ጃፓናዊ መፍትሔ አምጡ ነው ያላቸው፡፡ እንደዚህ የሚል አመራር እንዲመጣ ነው የእኔ ዓይነቱ ሰው የሚያስፈልገው፡፡ የእኛ ችግር ከዓለም የተለየ መድኃኒትና መፍትሔ የሌለው ነው እንዴ? ለኮሮና በሽታም እኮ ክትባት ተገኝቷል እንኳን ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ አያቅተንም፡፡ እኛ የከበደን መስማት ነው፡፡ የሚሰማና የሚያከብር፣ እንዲሁም ተቀባይ የሆነ መንግሥት ከፈጠርን ብዙ ችግር የለብንም ባይ ነኝ፡፡

ሪፖርተር፡– እንደ አንድ የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፓርላማው መካከል ያለውን መናበብ እንዴት ታየዋለህ? በሥራ አስፈጻሚና በፓርላማው መካከል ያለው ግንኙነትስ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- እስካሁንያለውንከሆነየምትለኝእንዴትአድርጎ?የለምእኮባህሉ፡፡የነበረው ባህልእኮነውመቀየርያለበት፡፡መቶበመቶየአንድፓርቲሰዎችናቸው፡፡እነዚህየአንድፓርቲሰዎችደግሞለውጥከመምጣቱበፊትየተመረጡ ናቸው፡፡የተመረጡበትንመንገድደግሞእያወቅነውእንዴትአድርጎይሆናል?እንዲሁምየጠቅላይሚኒስትሩጀግንነት፣ጉብዝናናብልኃትበቀጣዩፓርላማፍንትውብሎይወጣልብዬ ነውየምገምተውናየማስበው፡፡የተሻለይሠራሉ፣የተሻለይናገራሉ፣የተሻለያስባሉ፣የተሻለይተልማሉ፣ ወዘተየሚለውንቀጣዩፓርላማያሳያልየሚልእምነትአለኝ፡፡

ሪፖርተር፡– የሃይማኖትና የብሔር አክራሪነት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ይህን ጉዳይ እንዴት ታየዋለህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- የሃይማኖትናየብሔርአክራሪነትበኢትዮጵያእየሰፋመጣየሚሉአሉ፣አዎ፡፡የነበርንበትፖለቲካዊናማኅበራዊመዋቅርደግሞለእነዚህሰዎችነውየሚያግዘው፡፡እኔአንዱበቀጣይዓመትመሻሻልአለበትብዬየማስበውይህየፖለቲካናየባህልመዋቅርነው፡፡አሁንለምሳሌቢቻልሃይማኖትንመሠረትአድርገውፓርቲዎችመመሥረትየለባቸውምእንደተባለውሁሉ፣ብሔርንናአንድጎሳንመሠረትአድርጎፓርቲመመሥረትአይቻልምመባልአለበት፡፡ የሲቪክማኅበራትለምንአይሆኑም?የግድየብሔርፓርቲመሆንእኮየለባቸውም፡፡አብዛኞቹየሚገርምህየብሔርፓርቲይመሠርቱናሥራቸውየሲቪክማኅበርነው፡፡ትንሽነገርከሆነአካባቢወስደውሶሻልዴሞክራሲ፣አብዮታዊዴሞክራሲየሚልይጨምሩበታልእንጂመጨረሻላይጥያቄያቸውወደ ታችሲወርድመንገድአልተሠራም፣ውኃአልገባም፣መብራትየለም፣ማዳበሪያየለም፣ምናምንየለምነውየሚሉት፡፡ነገርግንይህየፖለቲካጥያቄአይደለም፡፡

ይህንን ጥያቄ ማኅበራት ሊመልሱት የሚገባ ነው፡፡ በተለይም ትልልቅ የሆኑ የገበሬ፣ የሠራተኛና የሲቪክ ማኅበራት ይህንን ጥያቄ ሊገፉ የሚችሉ ቢኖሩን እኮ እነሱ ናቸው እዚህ አካባቢ መንገድ፣ ውኃ፣ መብራት የለም ብለው መጮህ የነበረባቸው፡፡ ልክ እንደ ሌላው ዓለም እንደሚደረገው ሁሉ ማለት ነው፡፡ አሁን እኮ እዚህ አገር ያለው ጉዳይ ተቀላቅሎብናል፡፡ እዚህ አካባቢ መዋቅሩ መቀየር ያለበት ይመስለኛል፡፡ ብልፅግና ላይ አንዱ ቅልቅ ነገር ያየሁት ሒደት ቢያንስ አገራዊ ሆኖ ለመምጣት እየታገለ ይመስላል፡፡ ፓርቲዎች በመብዛታቸው የሲቪክ ማኅበራትን ቦታ ነው የያዙት፡፡ አሁን ለምሳሌ አንድ አካባቢ ያለ ጎሳ መብቴን አስከብራለሁ ይልና መጀመሪያ የሚታየው ፓርቲ መመሥረት ነው፡፡ ነገር ግን መብት ለማስከበር ፓርቲ ብቻ አይደለም የሚያስፈልገው፡፡ መብት ለማስከበር በጣም ብዙ መንገዶች አሉ፡፡ ነገር ግን እኛ አገር እንደ ፋሽን ስለተያዘ ዝም ብሎ የአንድ አካባቢ ሰው ተነስቶ የሆነ ፓርቲ ይመሠርታል፡፡ በነገራችን ላይ በዚህ ከቀጠለ የመርካቶ፣ የአራት ኪሎ፣ የስድስት ኪሎ፣ የየካ፣ የሰሚት፣ ወዘተ እያልን ፓርቲ በየሠፈሩ ይመሠረታል፡፡ በቃ ሁሉ ነገር የሚፈታው በፓርቲ ነው የሚል ድምዳሜ እናመጣለን፡፡ ስለሆነም ይህንን ነው ማስቆም ያለብን፡፡

ሪፖርተር፡– ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለውን የፌዴራሊዝም ሥርዓት እንዴት ታየዋለህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡– እኔሁለትቅርፅይዞመምጣትአለበትባይነኝ፡፡ይህማለትየብሔረሰቦችንጥያቄየሚመልስናየብሔረሰቦችንምማንነትየሚያገናኝመሆንአለበትብዬአስባለሁ፡፡ ‹‹አንድብሔርአንድመዋቅር››የሚለውለኢትዮጵያጠቃሚነውብዬአላስብም፡፡ለምሳሌትልልቅየሚባሉትክልሎችአራትወይምአምስትክልሎችቢሆኑምንይሆናሉ?ሁለትብሔሮችአንድክልልቢሆኑምንችግርአለው?ተመልከትአሁንሸዋውስጥብዙብሔረሰቦችአሉ፡፡ምንአለሸዋየሚባልክልልፈጥረንኦሮሚኛ፣አማርኛ፣ትግርኛ፣ጉራጌኛ፣እንዲሁምሌሎችንየያዘየሥራቋንቋያለውክልልብንመሠርት፡፡ለምንአማራብቻውን፣ኦሮሞብቻውን፣ከምባታብቻውንእንደክልልየሚቆጠረው?ይህአያዛልቀንም፣ድልድዩንማንይሥራው?

ሪፖርተር፡– ወደ ቀድሞ የክልል አጠራርና አሰያየም ማለት ነው?

ዲያቆን ዳንኤል፡– እንደክፍለ ሀገርሊሆንምላይሆንምይችላል፡፡ከእሱጋርማገናኝትየለብንም፡፡ቁጭብለንግንማሰብአለብን፡፡የግድአንድክልል፣አንድቋንቋየሚለውንመተውአለብን፡፡ብዙቋንቋዎችመናገርአለብን፣ባለብዙቋንቋነን፡፡የብሔረሰቦችንምመብትየሚያስከብር፣ግንደግሞየግድብሔርናአካባቢንየሚያገናኝ፣ቢቻልየክልሎችስያሜራሱእንደሌላስያሜወይምወንዝብለንእንደምንጠራውተብሎቢሰየም ይሻላል፡፡ከብሔርስያሜመውጣትአለብን፡፡ እግርኳስፌዴሬሽንበተለይምከክልልየሚመጡቡድኖችየጎሳስምይዛችሁእንዳትመጡነውያለው፡፡ስለዚህምነውፋሲልከነማ፣ሆሳዕናከነማ፣አዳማከነማ፣ወዘተእየተባለየተመጣው፡፡

ሪፖርተር፡– ስለቀጣዩ ምርጫ ሲሰማ አገራዊ መግባባት ሳይመጣ ወደ ምርጫ መግባት አደጋ አለው፣ በመሆኑም አገራዊ መግባባት ይቅደም የሚሉ ፓርቲዎች አሉ፡፡ አገራዊ መግባባት በዚህ አጭር ጊዜ መምጣት ይችላል?

ዲያቆን ዳንኤል፡– አገራዊ መግባባት እኮ እንደ ፊዚክስ ወይም ኬሚስትሪ በቀመር የምትሠራው፣ ወይም እንደ ገንዘብ ቆጥረህ የምትደርስበት አይደለም፡፡ መቼ ነው ይህን የምናመጣው? የተለያየ ዓይነት አቋም ያለን አካላት ነን፡፡ መግባባት የተሳናቸው የፖለቲካ ፓርቲዎችን እኮ እናያለን፡፡ ሁልጊዜ ምርጫ ቦርድ ሲዳኝ የሚውለውን እናያለን፡፡ ይልቁንስ ለመግባባት የማያስችለንን ሰንኮፍ መጀመርያ እንንቀለው፡፡ ያላግባባን ምን ነበር የሚለውን እንለየው፡፡ ያላግባባን እኮ የፖለቲካና የማኅበራዊ አወቃቀራችን ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ምርጫ ይለፍና ቁጭ ብለን እንነጋገራለን፡፡

ሪፖርተር፡– ስለዚህ አገራዊ መግባባት ከምርጫው በፊት አይታሰብም?

ዲያቆን ዳንኤል፡- አዎ! መጀመርያ የሕዝብ ውክልና ያገኘው ይታወቅ፡፡ ይህ ፓርቲ ሕዝብ የወከለው ነው የሚለውን በምንድነው የምናውቀው? እስኪ ያሸንፍና ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ወክሎኛል ብሎ ይምጣ፡፡ ከዚያ እውነትም ያኔ ሕዝቡ ወክሎታል ይባላል፡፡ ‹‹ሕዝብ ተናገርልኝ በከንፈሬ፣ ተቀመጥ በወንበሬ›› ብሎኛል ይበልና በሕዝብ ከንፈር ነው የምናገረው ብሎ ይምጣ፡፡ ዝም ብሎ ስለተሰበሰበና ምርጫ ቦርድ በእነ እንትና መዝገብ ብሎ ስለመዘገበው ብቻ እንዴት ነው አገራዊ መግባባት ላይ እንነጋገር የሚባለው? እስኪ ሕዝቡ ይወክለውና ይናገርልኝ ይበለው፡፡ ከዚያ ሕዝቡ ሲመርጠው ወደ መነጋገር ይገባል፡፡

ሪፖርተር፡– የኢትዮጵያን የቀደመ ታሪክ እንሠራለን የሚሉ ፓርቲዎች እየመጡ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የቀደመ ታሪክ ለአንተ ምንድነው?

ዲያቆን ዳንኤል፡– የተለያየ ዓላማ ይኑረው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ላብድ ነው ብሎም ይምጣ፣ ከዚያ ተሰብስቦ ፓርቲ ይመሥርት፣ ከዚያ ይበድ ብሎ ሕዝቡ ይምረጠው፣ ከዚያ መጥቶ ይሟገት፣ ዋናው ግን የሕዝብ ድምፅ ያግኝ፡፡ መፈተኛ እኮ ነው ይኼ፡፡ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነህ ዩኒቨርሲቲ እንደምትገባው ሁሉ የፖለቲካ ፓርቲም ይፈተን፣ እንየውና በዚያ ይለፍ፡፡

ሪፖርተር፡– ወደ ፖለቲካ ሕይወት እየገባ እንዳለ ሰው እንደ አገር የሚያሳስብህ ነገር ምንድነው?

ዲያቆን ዳንኤል፡– እውነት ለመናገር እኔ ብዙም እንደ አገር የሚያሳስበኝ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን አለመሥራታችን ነው የሚያሳስበኝ፡፡ ማለትም ያለንን ዕድል ተጠቅመን ለሥራ አለመሠለፋችን ግን ያሳዝነኛል፡፡ ብዙ ልንሠራው የምንችለው ጉዳይ እያለ፣ ብዙ ሀብትም እያለን፣ ብዙ ዕድልም እያለን ጊዜው በወሬና በሽኩቻ ማለቁ፣ ምንም በማይጠቅሙ ጉዳዮች ማለቁ ያሳስበኛል፡፡ አንድ ሰው ለሽሮ፣ ለበርበሬ፣ ለእንጀራ የሚያወጣውን ጊዜ ለፈንዲሻ አያወጣም፡፡ የትኛውም ቤት ብትገባ ፈንዲሻውን ይተወዋል እንጂ ሽሮውን አይተውም፡፡ እኛ ግን ሽሮውን ትተን ፈንዲሻው ላይ ነው ያለነው፡፡ ፈንዲሻ ምን ያደርጋል? በዚህ ሰዓት ቢቀርስ? በእርግጥ ደስ ይላል፡፡ ፍንድትድት ብሎ ቤቱን በሙሉ ነጭ በነጭ ሲያደርገውና ኩርሽም፣ ኩርሽም ስታደርግ ደስ ይላል፡፡ ግን ምን ይሆናል? ፈንዲሻ ብቻውን ወጥ አይሆን፣ እንጀራ አይሆን፣ ግን ሊያስደስት ይችላል፡፡ ከዚያ ያለፈ ነገር ምንም ሊያመጣ አይችልም፡፡ ፈንዲሻ ከበላህ በኋላ ሽሮ ትፈልጋለህ፣ እንጀራ ትፈልጋለህ፡፡ ስለዚህ እኛ መቅደም የነበረበትን ባለማወቅ የፈንዲሻ ፖለቲካ እየተጫወትን ሰነፍ አገር ልናደርጋት ነው፡፡ እናም አያሠጋኝም፣ ነገር ግን ያሳስበኛል፡፡

ሪፖርተር፡– ኢትዮጵያ ውስጥ አላባራ ያለው ግድያ፣ ግጭትና መፈናቀል በምን ምክንያት የመጣ ነው? በተለይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ይህ ችግር ምን ያሳያል?

ዲያቆን ዳንኤል፡- ያውሊነጋሲልይጨልማል፡፡ላለፉትበርካታዓመታትእኮየአገሪቱብሎንሲላላነበርየቆየው፡፡አሁንትንሽበሄድክቁጥርአንድብሎንይወድቃል፣እልፍባልክቁጥርሌላውብሎንእየወለቀ ነው፣ግንእንደላላእንኳንአታውቅም፡፡አሁንእኮየተያዘውማጥበቅነው፡፡እናምአሁንያለውችግርብሎንበሚያላሉናበሚያጠብቁሰዎችመካከልያለግብግብ ነው፡፡ሁሉንምብሎንደግሞአታገኘውም፡፡ተቆጥሮ በሰነድ የተቀመጠነገርስሌለነውአሁንየቸገረን፡፡እያለፈሲሄድግንለዚህማገዶየሚሆነውእንጨትእያለቀ፣በፊትየገባውእንጨትእየነደደሲሄድናእሱእንጨትሲያልቅተጨማሪእንጨትስለማይመጣእንደአዲስአጥብቀንእናቆመዋለን፡፡

ሪፖርተር፡– የአንተ ወደ ፖለቲካ መግባት ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ጋር ምን ዓይነት ቁርኝት ይኖረዋል?

ዲያቆን ዳንኤል፡- እኔየገባሁትለኢትዮጵያስልነው፡፡ኢትዮጵያስትጠቀምኦርቶዶክስይጠቀማል፡፡ኢትዮጵያስትጠቀምእስልምናይጠቀማል፣ፕሮቴስታንትይጠቀማል፡፡ኢትዮጵያካልተጠቀመችማናችንምአንጠቀምም፡፡አንድመርከብላይእየሄድንመርከቡላይባለውጉዞሳሎን፣መኝታቤትወይምበረንዳየምትለውመጀመርያመርከቡሲንቀሳቀስነው፡፡መርከቡእየሰመጠሳሎኑም፣አልጋውም፣በረንዳውም፣ምንምዓይነትደረጃላይብትሆንከመስመጥአትድንም፡፡ይህየፖለቲካነፃነትለብዙየሃይማኖትሰዎችትልቁነፃነትነውብዬአምናለሁ፡፡

ሪፖርተር፡– ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ችግር ትልቁ ምክንያት ምንድነው ትላለህ?

ዲያቆን ዳንኤል፡- የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አወቃቀሯ ነው፡፡ ከዚህ የመነጩ ችግሮች ናቸው ብዙዎች የምታያቸው፡፡ የተዋቀርንበት ነገር ከኢትዮጵያ ጋር አልሄድ አለና አላርጂ ሆነባት፡፡ ችግሮቻችን የፈታን መስሎን ከኢትዮጵያ ጋር የማይሄድ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አወቃቀር ይዘን መጣን። መጀመርያ ያጠገበን መሰለን አሁን ግን እያሳከከን መጣ፣ ምክንያቱም አልቻልንም።

ሪፖርተር:– ከአገሪቱ አጠቃላይ ችግሮች በመነሳት ከመንግሥት ዕርምጃና ከማኅበራዊ የትስስር ገጾች ሁኔታ አኳያ ምን ይታይሃል?

ዲያቆን ዳንኤል፡– በዚህ ከቀጠልን ለሰከንድ አንድ ሰው የአዕምሮው ጤናው ሲናጋ መጨረሻው የሥነ አዕምሮ ሆስፒታል ውስጥ እንደሚሆን ሁሉ፣ የእኛም መጨረሻ እንደዚያ ይሆናል። ማለትም አገራዊ የሥነ አዕምሮ ሆስፒታል እንደርሳለን በመጨረሻ፡፡ በመሆኑም ለዚህ ቀድመን ማሰብ አለብን፡፡ ነገር ግን እኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አምናለሁ፣ ፖለቲከኞችን አይደለም የማምናቸው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ታግሶ ታግሶ ተው ይላል፣ መጨረሻ ላይ መሠረቱን የሚያናጉበት ከመጡ እንቢ ስለሚል አንድ ቀን ይነሳል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ አሁን እየጎበጠም ቢሆን ልጆቼ ብሎ ተሸክሟቸዋል፡፡ አንድ ቀን የማይሆን ነገር ውስጥ ሲገቡ ግን አሽቀንጥሮ ነው የሚጥላቸው፡፡ ሲጥል ደግሞ አይቼዋለሁ። ዕብደታቸው ወደ አገር ማጥፋት ሲሄድ ሕዝብ ዝም ብሎ አይመለከትም።

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//iphumiki.com/4/4057774