Press "Enter" to skip to content

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተነሳው ውዝግብ የስራ አመራር ቦርድ እና የኡለማ ሳይሆን በኡለማ ውስጥ ባሉ ጥቂት ግለሰቦች የተፈጠረ መሆኑን የስራ አመራር ቦርዱ አስታወቀ፡፡

በኡለማው እና በስራ አመራሩ ዘንድ አለመግባባት እንደተፈጠረ ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን ስራ አመራር ቦርዱ ለአሀዱ አስታውቋል፡፡መጅሊሱን እና የጠቅላላ ጉባኤው እንዳይደረግ የፈለጉት በኡለማ ውስጥ ያሉ ጥቂት ግለሰቦች መሆናቸውን የቦርዱ አባል ዶክተር ጀማል መሐመድ ከአሀዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የስራ አመራር ቦርዱን ማገድ የሚችለው ጠቅላላው ጉባኤ ሲሆን እገዳውን አድርገናል ያሉት ከአምስት የማይበልጡ ግለሰቦች እንደሆኑም ዶክተር ጀማል ተናግረዋል፡፡ዋነኛው የአለመግባባት ችግር ጠቅላላ ጉባኤ ይደረግ የሚለው ጥያቄ ለፕሬዝዳንቱ የቀረበ ቢሆንም ምላሽ ስላልተሰጠበት ነው ብለዋል፡፡

የስራ አመራር ቦርዱም ስብበሳውን ወይም ጠቅላላ ጉባኤውን ህግን ጠብቆ ምላሽ በማጣቱ እንዳደረገው ገልጸዋል፡፡የቦርዱ ፍላጎት ሙፉቲውን ከስልጣን ማስነሳት ነው የሚለው ሀሰተኛ መረጃ ነው ብለውታል፡፡በጠቅላይ ምክር ቤቱ በአንዳንድ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እና ውንጀላን በሚመለከትም የጠቅላላ ምክር ቤት የስራ አመራር ቦርዱ ለህግ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡

ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ማህተም ሰርቀው ቢሮ ሰብረው የመገናኛ ብዙሃንን ጠርተዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ዶክተር ጀማል መሐመድ የተናገሩ ሲሆን ይህ ህገ ወጥ ውንጀላ በህግ ፊት ቀርቦ መታየት አለበት የሚለው ስለታመነበት ወደ ጉዳዩ ለህግ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡

ቢሮ ተሰብሯል ማህተም ተሰርቋል የሚለው ውንጀላ ሀሰት ነው ከዚህ ቀደም የምንጠቀምበትን ቢሮ ያሸጉት ውንጀላ ያቀረቡት ግለሰቦች ናቸው ሲሉ የስራ አመራር ቦርድ ፀኃፊ አቶ ከማል ሀሩር ገልጸዋል፡፡የስራ አመራር ቦርዱ የተጠቀመው ማህተም ህጋዊ እና ከ30 እስከ 40 አመት አገልግሎት ላይ የነበረ መሆኑን ተናግረዋል፡ አሐዱ ራድዮ 94.3

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//naucaish.net/4/4057774