ኢትዮጵያና ኒጀርን የሚያመሳስሏቸው ነገሮች ከብዙ በጥቂቱ

ኢትዮጵያና ኒጀርን የሚያመሳስሏቸውን ጥቂት ነገሮች ጀባ እንበላችሁ። አለመታደል ሆኖ እንበልና ኒጀርም ልክ እንደ ኢትዮጵያ በደረቅ ምድር የተከበበች Land Locked Country ነች። አሁንም እንደ አለመታደል ሆኖ ኒጀርም ልክ እንደ ኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ሀብቶች እያላት ግን በድህነት እና በብድር እዳ ከተዘፈቁ የአፍሪካ ሀገራት ዋነኛዋ ነች። ዩራኒየም የተባለው የተፈጥሮ ንጥረ ነገር በብዛት የተሸከመች ባለጸጋ ነች።

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዟ እንደምትኮራው ሁሉ ኒጀርም ስሙን በወረሰችው ታላቁ የኒጀር ወንዝ በአለም ትታወቅበታለች። ይሁን እንጂ በኒጀር ወንዝ ላይ ብዙም የልማት ተጠቃሚ እንዳልሆነች ይነገራል። እንድያውም የኒጀር ወንዝ በሚሞላበት ወቅት በየአመቱ በርካታ ዜጎቿን ህይወት ይቀጥፋል። ሌላው ኢትዮጵያና ኒጀርን የሚያመሳስላቸው ባሏቸው ቆነጃጅት ነው። ኒጀራውያን ሴቶች ልክ እንደ ኢትዮጵያውያኑ እንስቶች ደመ ግቡና ቆንጆ መሆናቸው በአፍሪካ ግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *