በውጭ የሚገኙ ልብሰ ተክህኖ ለባሽ የትህነግ ካድሪዎች መንጫጫትና መወራጨት

ትህነግ የፖለቲካ ዓላማዋን ለማሳካት አስቀድማ ከዘመተችባቸው ኢትዮጵያዊ ተቋማት መካካል አንዷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ ይታወቃል። ትህነግ ካድሬዎችን መልምላ በጸረ-አማራና በጸረ-ኦርቶዶክስ ጥላቻ አሰልጥና ልብሰ ተክህኖ አልብሳ በየቤተክርስቲያን ውስጥ እያሾለከች ያስገባቻቸው ካድሬዎች በቤተክርስቲያኒቷ ላይ ያደረሱት ጥፋትና ጉዳት ሁልቆ መሳፍርት የለውም።

ትህነግ የቤተክርስቲያኒቷን ቅርሶችና መጻህፍት በመዝረፍ፣ አገር ወዳድ ካህናትን በመግደል፣ ቤተክርስቲያናትን በማርከስና የጦርነት ማዕከል በማድረግ፣ ምህረት የሌለው ወንጀል ፈጽማለች።

ከዚህም በላይ ህጋዊውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው በማውረድ በካድሬና በቀማኛው አባ ገብረመድህን ከመተካቷም በላይ ባህታዊ አባ ፍቃደ ስላሴ የተባሉ ታላቅ አባትን ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ደማቸው አፍሳለች። ከዚህም በተጨማሪ የዋልድባን ገዳም በመድፈር የገዳማዊያንን መኖሪያ ቤቶችንና መካነ መቃብራትን በግሬደር በማረስ አፅማቸውን ከቆሻሻ በመደባለቅ እንዲሁም ተዘርዝረው የማያልቁ እንደውም አንዳንድ ምዕመናን እንደሚሉት በአገሪቱ ታሪክ ተመዝግቦ የማያውቅ ወንጀል በኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ፈጽማለች።

በኢትዮጵያዊያን ላይ ከላይ የተጠቆሙት ወንጀሎች ሲፈጽሙና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና አማራ መውደም አለባቸው ተብለው በትህነግ ሲቀጠቀጡና አሳራቸውን ሲያዩ አብረው ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ልብሰ ተክኖ ለባሽ ካድሬዎች ትህነግ ከፖለቲካ ሥልጣን ከተገለለበችበት ጊዜ አንስቶ ሲወራጩና ሲቁነጠነጡ መቆያታቸው ይታወቃል።

ይባስ ብለው በቅርቡ “የትግራይ ካህናት” የሚል ከትግራይ ምእመናን ጋር ምንም ግንኙነትና ውክልና የሌለው የሀሰት ስም ለራሳቸው በመስጠት የለመዱትን እኩይ ተግባር ቀጥለውበታል። እነዚህን ካድሬዎች አስመልከተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ያስተላለፉትን መልዕክት አቅርበንላችኋል። መረጃ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *