ይህ ሰው – ጆን ሙጉፉሊ ማን ነው?

እንደ አዎሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 በተደረገ ምርጫ አሸንፎ ወደ ስልጣን የመጣው የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ፖምቤ ሙጉፉሊ በስልጣን በቆየባቸው አመታት ያደረጋቸው ተግባራትና የተጋፈጣቸው ፈተናዎች

ሙጉፉሊ ገና ወደ ስልጣን እንደመጣ በመጀመርያ ያደረገው ነገር እንደ መሪ በቤተ መንግስት ወይም በየቢሮው ተቀምጦ ወንበር ማሞቅ አይገባም በማለት ሸሚዙን አጣጥፎ የታንዛኒያን ጎዳናዎች በማጽዳት ባለስልጣናቱም ይህንን ልማድ አድርገው ለህዝብ ምሳሌ እንዲሆኑ አደረገ። ከዝያም ባለስልጣናቱ በሆነ ባልሆነ ምክኒያት ወደ ውጭ ሀገር የሚያደርጉትን ቅጥ ያጣ ጉዞ እንዲቀንሱ ሲልም እንዲያቆሙ ህግ አወጣ።

ከሁሉም በላይ ደግሞ በበርካቶች የተወደደለትና የተደነቀበት ነገር በየአመቱ ከመንግስት ካዝና ለበአል እየተባለ የሚመዠረጠውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መገደቡ ነው። በዚህም ለገዛ ፓርቲው አመታዊ በአል አከባበር ለቲሸርት፣ ለኮፊያና ለውሀ እንዲሁም ለጠቅላላው የበአል ወጪ ወደ መንግስት ካዝና እንዲገባ አስችሏል።

ሙጉፉሊ ይበልጥ የሚጠቀስበት ደግሞ የመንግስት ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸው በሙሉ በመንግስት የጤና እና የትምህርት ተቋማት እንዲጠቀሙ ማድረጉ ነው። በዚህም ልጆቻቸውን ወደ አውሮፓና አሜሪካ እየላኩ በሚሊየን ዶላር ወጪ የሚያስተምሩ ባለስልጣናትን በመቆጣጠር እነሱም ልክ እንደ ሌላው ማህበረሰብ በራሳቸው በሚተዳደሩ ተቋማት እንዲጠቀሙ አስችሏል።

ሙጉፉሊ ምንም እንኳ ቡልዶዘር እየተባለ በርካታ ያረጁ አስተሳሰቦችን እያፈራረሰ የታንዛኒያ ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ ቢያደርግም ቅሉ ይህ ድርጊቱ በብዙዎች ዘንድ አልተወደደለትም።

በተለይም ለተመሳሳይ ጾታ ጥብቅ ህግ ማውጣቱ እንዲሁም የውጭ ሀገራት እርዳታና ድጎማን ተቀዳሚ ምርጫው አለማድረጉና ሌሎች ምክኒያቶች ለሙጉፉሊ መልካም ነገር እንዳላመጣለት ይነገራል። ሙጉፉሊና የምዕራቡ አለም የገቡትን ፍጥጫና እንካ ሰላንትያን በተመለከተ ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ ያገኘነው ከኒው አፍሪካ ነው። ይመልከቱት

EU recalled Its ambassador to Tanzania over Magufuli’s LBGT Crackdown. Magufuli Skipped the UN General Assembly! Magufuli denounced UN human rights report.

Magufuli banned all foreign trips for public servants. Magufuli deported UNDP CR Head. Magufuli deported Head of EU Delegate to Tanzania. European Union Stopped its Financial Support to Tanzania.

Magufuli Denounced EU-East African Trade Deal as a form of Neocolonialism. European Union declares Magufuli a Dictator. Magufuli Refuses to bow to New World Order.

Magufuli refuses to put Tanzania under WHO Covid-19 guidelines. Magufuli declares Cov*d a Scam.
Magufuli refuses to Take Loans and grants from World bodies to deal with Covid-19.

Magufuli Welcomes Madagascar’s traditional Vaccine for covid. Magufuli refuses that Tanzania will not order or buy any Covid -19 Vaccine from the West or anywhere.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *