የቢቢሲ ዘጋቢ በኢትዮጵያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር ዋለ

ግጭት በተካሄደበት የሰሜናዊ ኢትዮጵያዋ የትግራይ ክልል የቢቢሲ ዘጋቢ የሆነው ግርማይ ገብሩ በአገሪቱ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ውሏል። ለቢቢሲ የትግርኛ ቋንቋ አገልግሎት የሚሰራው ግርማይ ገብሩ የተያዘው በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ በሚገኝ ካፍቴሪያ ውስጥ ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር ነው።

የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት አምሰቱ ሰዎች የተያዙት ወታደራዊ የደንብ ልብስ በለበሱ ወታደሮች ሲሆን፤ በሁለት የወታደር ተሽከርካሪዎች በታጀበ መኪና
መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

ግርማይን ጨምሮ አምሰቱ ሰዎች ለምን ተይዘው እንደተወሰዱ ግልጽ አይደለም። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ሪፖርተሩ መቀለ ውስጥ ወደሚገኝ
ወታደራዊ ካምፕ ተወስዷል።.

ወደ ክልሉ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ለወራት እንዳይገቡ ከተከለከለ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ አገር ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ገብተው እንዲዘግቡ ባለፈው ሳምንት ፈቅዷል።

የቢቢሲው ዘጋቢ የታሰረው ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) እና ለፋይናንሻል ታይምስ የሚሰሩ ሁለት ሌሎች ጋዜጠኞቹን የሚያግዙ ባለሙያዎች (ፊክሰር) መታሰራቸው ከተነገረ ከቀናት በኋላ ነው።

ሌላ ታምራት የማነ የተባለ የአገር ውስጥ ጋዜጠኛም ባልታወቀ ምክንያት በወታደሮች ተይዟል። ባለፈው ሳምንት አንድ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ባለስልጣን “አሳሳች በሆኑ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ላይ መንግሥት እርምጃ ይወስዳል” ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *