ዐጤ ምንሊክ ፎቶ የተነሱባት ካሜራ ‘በሕይወት ተገኘች’

አልፍሬድ ኢልግ የሚባል የስዊዝ ሰው አጤ ምንሊክን ለማግኘት ከዙሪክ ተነስቶ አንኮበር በገባ ልክ በመቶ አርባ ዓመቱ፣ እኔ የአልፍሬድን የልጅ ልጆች ለማግኘት ከናይሮቢ ዙሪክ ገባሁ።

አልፍሬድ ያኔ ከዙሪክ- አንኮበር ለመግባት ድፍን 8 ወራት ወስዶበት ነበር። እኔ ከናይሮቢ ዙሪክ ለመግባት ድፍን 8 ሰዓት እንኳ አልወሰደብኝ። አንዳንድ ነገሮች ግን በዘመን ርዝማኔ እምብዛምም አልተለወጡም፡፤ ኢልግና ምንሊክ ከ102 ዓመት በፊት ያነጠፉት ባቡር ከለገሀር ተነስቶ ወደ ‘ባሕረ ነጋሽ’ አልለጠቀም። በጣርማ በር ሰንጥቆ ደብረ ብርሃን አልዘለቀም።

ከ102 ዓመት በኋላም ኢልግና ምንሊክ በተገናኙባት በአንኮበር የሚያልፈው ሎንቺን እንጂ ባቡር አይደለም። ዐጤ ምንሊክ አንድ አፍታ ካረፉበት ከታዕካ ነገሥት ባኣታ ለማርያም ቀና ብለው ባቡሩን ቢያዩት፤ አልፍሬድ ኢልግም አንድ አፍታ ከዙሪክ ፍሪድሆፍ ኢንተንቡል መካነ መቃብር ቀና ብሎ አንኮበርን ቢመለከት…ሁለቱም ሸለብታ ወስዶን እንጂ…መቼ ሞትን ይሉ ነበር?

ቀላል ባቡር ስል ያሬድ ኃይለሥላሴ ታወሰኝ። ልበ ቀናው ያሬድ ኃይለሥላሴ። ዙሪክ ያለው ያሬድ ኃይለሥላሴ። በእናቱ ስዊዛዊ በአባቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊው፤ ያሬድ። ተወልዶ ያደገው እዚያው ነው። አፉን የፈታውም በጀርመንኛ ነው።

ታዲያ ይሄ ያሬድ የሚባለው ልጅ፣ “ከቀላል ባቡሩንና ከአልፍሬድ ኢልግ ጋር ምን አገናኘው?” ትሉ ይሆናል፤ ጥሩ ጥያቄ ነው። ሦስቱን የሚያገኛኘው የታሪክ መስመር የሚከተለው ነው።

ያሬድ ከዕለታት አንድ ቀን በአገሩ ዙሪክ ቀላል ባቡር በተሳፈረበት አጋጣሚ እንደ ሁልጊዜው መጽሐፍ ያነብ ነበር። አጠገቡ አንዲት በዕድሜ ጠና ያሉ ሴትዮ ገልመጥ እያሉ ይመለከቱታል። እርሱም በግማሽ ልብ ንባቡን ቀጥሏል። ሙሉውን መረጃ እዚህ ይመልከቱ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *