አስቂኙ የአረና መግለጫ

አረና ፓርቲ በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋሉ መሬቶቻችን ይመለሱ ሲል ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፓርቲው ዛሬ ባወጣው ዝርዝር መግለጫው ላይ ቀድሞ በትግራይ ክልል የነበሩ መሬቶች በአስቸኳይ ይመለሱ ሲል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮችም ክልሉን ለቀው ይውጡ ሲል ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል አረና እዝያው መቀለ ተቀምጦ ባለፉት ሶስት ወራት በተካሄደው የህግ ማስከበር የተፈጸሙ የህግ ጥሰቶችን በራሱ ተዘዋውሮ አጣርቶ መረጃውን ማቅረብ ሲገባው “የኤርትራ ሰራዊት በተለይ የህዝቡን ሀብትና ንብረት በማሸሽ የቀረውንም በማውደም ከፍተኛ ጥፋት መፈጸሙ እየተነገረ ነው በማለት ከሶስተኛ ወገን የሰማውን በስማ በለው አቅርቧል፡፡

በአሁን ወቅት በትግራይ ጉዳይ ከአለማቀፍ ሚዲያዎች ጀምሮ እስከ ታች የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች በርካታ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ እንዲሁም የተጋነኑ ሪፖርቶች እየቀረቡ ህዝቡ እየተደናገረና ሊረዱ የሚገባቸው ዜጎች ትክክለኛውን እርዳታ እንዳያገኙ ተጨማሪ ተግዳሮት በመሆን ላይ ናቸው፡፡

ይህን ችግር ለመቅረፍ በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ውስጥ ራሱን ያካተተው አረና ፓርቲ ጉልህ ሚና መጫወት ተስኖት የሌሎችን ኡኡታ ብቻ በማስተጋባት ወደ እውነቱ እንዳንቀርብ ማድረጉ የሚያስተዛዝብ ነው፡፡

የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ የምንሸሸውና የማንፈልገው ጦርነት በትግራይ ተከስቷል፡፡ ይህን ሁኔታ ለማስቀረት ብዙ ጥረት መደረግ ነበረበት፡፡ ኝ አልሆነም፡፡ ጦርነቱን ማስቀረት ባይቻል እንኳ ከጦርነቱ በኋላ ሊደረግ የሚገባውን ድጋፍና እርዳታ ለማፍጠን ያለምንም የፖለቲካ ወገንተኝነት እውነተኛውን የህዝብ ጉዳት አጥርቶ ለማቅረብ ከአረና ትግራይ በላይ ማን ይኖር ነበር? አረናም የህወሀት ጁንታን ጆሮ የሚያደነቁር የዲጂታል ወያኔን መረጃ ለቃቅሞ ለመግለጫ ማብቃትስ ሌላ ስጋትና ፍርሀት አይጭርም?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *