በ1902 ዓ.ም. በአሜሪካ ውስጥ “ምኒልክ ሊመጡ ነው” የሚል ዘገባዎች ይወጡ ነበር።

በ1902 በአሜሪካ ውስጥ “ምኒልክ ሊመጡ ነው” የሚል ዘገባዎች ይወጡ ነበር። በወቅቱ በአሜሪካን አገር አለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ለማዘጋጀት ከሴንት ሉዊስ ከተማ ወጣ ብሎ ሠፊ ጫካ እየመነጠሩና ሕንፃዎችን እየገነቡ ዝግጅቱን ማጣደፍ እንደጀመሩ፣ ለመጋበዝ ካሰቧቸው የዓለም ታዋቂና ታላላቅ ሰዎች መሀል ምኒልክ አንደኛው ነበሩ።

የካንሰሱ “ዘ ቶፒካ ስቴት ጆርናል” የምኒልክንና የጣይቱን ፎቶ አስደግፎ “አሜሪካንን የሚጎበኙት ንጉሠ ነገሥት” በሚል ርዕሰ ሠፊ ሀተታ አቅርቦ ነበር። ምንጭ ታላቁ ጥቁር፣ በንጉሤ አየለ፣ ገፅ 104

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *