ከጭነት ጋር ተመሳስሎ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባው መሳርያ

መነሻውን ጎንደር ያደረገ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከጫነው ጭነት ጋር በማመሳሰል 2 ብሬን ፣ 2 ስናይፐር ፣ 38 ትልቁ እና 25 ትንሹ ኢኮልፒ ሽጉጦች 5992 የክላሸ ኮቭ ጥይት 892 የኢኮልፒ ሽጉጥ ጥይት 5 የስናይፐር ጥይት ፣ የብሬን እግር እና ሁለት የብሬን ዝናር የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያደረገውን ክትትል መሰረት በማድረግ በጉሌሌ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መንደር ሰባት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የካቲት 19 ቀን 2013 ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በተሽከርካው ላይ ከተፈጨ የፕላስቲክ ምርት ጋር በማመሳሰል የጦር መሳሪያውንና ጥይቶቹን ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ለማስገበት ቢሞከርም በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል አዲስ አበባ ውስጥ መያዝ እንደተቻለ ብስራት ራዲዮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ህገወጥ የጦር መሳሪያውን ሲያዘዋወሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው እየተጠራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆ የጦር መሳሪያ ዝውውሩ እየተራቀቀ መምጣቱንና በቁጥጥር ስር የዋለው የጦር መሳሪያ ጭነት በማስመሰል ወደ አዲስ አበባ መግባቱን መረዳት ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *