ባንኩ ባለ ጸጋዎችን ብቻ ለማገልገል ሳይሆን ደሀዎችን ባለጸጋ ለማድርግ አስቦ የተነሳ ነው – አቶ መላኩ ፈንታ

የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በአዲስ አበባ የመጀመሪያ የምሥረታ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡ በምሥረታ ጉባዔው የአክሲዮን ማኅበሩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ እንደተናገሩት አማራ ባንክን የማቋቋም ሃሳብ የብዙዎችን ልቦና ያስተሳሰረና ያዘመደ ነው ብለዋል፡፡

የአክሲዮን ማኅበሩ ወደ ሥራ መግባት በበርካቶች ልቦና የነበረውን የመልማት ፍላጎትና የተቋም ግንባታ ውጥን እውን እንዲሆን ያስቻለ ወርቃማ እንቅስቃሴ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

‹‹ባንኩን የማቋቋም ሀሳብም ድንገት የመጣና ቅፅበታዊ ድርጊት አይደለም›› ያሉት አቶ መላኩ ለኅብረተሰብ ለውጥ ሲታሰቡ ከነበሩ በርካታ የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ቀዳሚ ሀሳብ ነው ብለዋል፡፡

የአክሲዮን አባላቱ ከቅድመ መስረታው ጀምሮ እስከ ስም አወጣጥ የተሳተፉበት፤ ሀሳባቸውን ያስተሳሰሩበት ድንቅ የአዕምሮ ውጤት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎችና አካባቢዎች አማራ ባንክ የእኔ ነው በማለት አክሲዮን በመግዛት፣ በሃሳብ በመደገፍና ባንኩን በመቀላቀል የአማራ ባንክ እንደ አማርኛ ቋንቋ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መተሳሰሪያ፣ መግባቢያና መገናኛ መድርክ እንዲሆን ለአደረጉት አባላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *