በትግራይ ከ800 ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል በህገወጥ መንገድ ወጥቶ ሊጓጓዝ ሲል ተያዘ

የፌዴራል መንግስት ለሽሬ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ዕርዳታ እንዲውል የላከው ከ800 ኩንታል በላይ እህል በህገ-ወጥ መንገድ ወጥቶ ሊጓጓዝ ሲል መያዙን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሽሬ ከተማ የጸጥታ ስምሪት አስታወቀ። ህገ-ወጥ ድርጊቱ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 10 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሽሬ ከተማ የጸጥታ ስምሪት ሃላፊ ሻለቃ አብርሃም አረሩ እንደገለጹት ለመከላከያ ሃይሉ በተሰጠው ጥቆማ መሰረት ለህዝቡ እንዲውል የተላከው እህል በህገ-ወጥ መንገድ ተጭኖ ወደ ሌላ ቦታ ሊጓጓዝ ሲል ተይዟል፡፡ከወንጀሉ ጋር የተጠረጠሩ ሰባት ግለሰቦችንና ሶስት አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሻለቃ አብርሃም ጠቁመዋል፡፡ መንግስት ለህብረተሰቡ የላከው ሰብዓዊ ድጋፍ በትክክል መድረስ አለበት ያሉት ሻለቃው ተረጂዎች የወሰዱትን እህል ለፍጆታ መጠቀም እንጂ አውጥተው መሸጥ የለባቸውም ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *