ኢትዮጵያ እንቁላል ከውጭ ሀገራት ማስገባት ልትጀምር ነው

ዩክሬን ከፍተኛ የሆነ የእንቁላል ምርትን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረሷን አስታዉቃለች፡፡ ኢትዮጵያ እና ዩክሬን በእንቁላሎቹ ጥራት ዙሪያና ወደ ኢትዮጵያ በሚልኩበት አግባብ ዙሪያ ተወያይተዉ መስማማታቸዉን ዩኬ አር ኢንፎረም የተሰኘ የአገሪቱ ሚዲያ በድረገጹ አስነብቧል፡፡

ስምምነቱ በዘርፉ የተሰማሩ የዩክሬን ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ የገበያ መዳረሻ እንዲያገኙም ያስችላል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ጥራት ያላቸዉ ዕንቁላሎችን ከዩከሬን በማስገባት ለምግብ ፍጆታ እንደምታዉልም ታዉቋል፡፡ ዩክሬን ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በሌሎች አፍሪካ አገራትም የእንቁላል ምርት በገፍ እንድምትልክ አስታ ዉቃለች፡፡ በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ፤ ጋና፤ ሞሮኮ፤ አልጄሪያ፤ አንጎላና ደቡብ አፍሪካ እንቁላል እንደምታስገባ ተሰምቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *