ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት ዳውድ ኢብሳ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ ኦነግ አይደለም – የኦነግ ህዝብ ግንኙነት
By: Date: February 22, 2021 Categories: ዜና Tags:

ኦነግ ከምርጫ 2013 ወጥቷል ተብሎ በማህበራዊ ትስስር ገጺ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ፓርቲውን የማይወክል እንደሆነ ተገለጸ፡፡ በ2013 ምርጫ ለመሳተፍ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዊች በምርጫ ቦርድ የምርጫ ማስፈጸሚያ ሰሌዳ መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ መጀመራቸው ይታወቃል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከምርጫው ወጥቷል፤ ተሳታፊም አይደለም እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ምን ያህል እውነት ነው ሲል አሐዱ ፓርቲውን ጠይቋል፡፡

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለአሀዱ እንደገለጹት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከፓርቲው ራሳቸውን ማግለላቸውንና በምርጫው ተሳታፊ አይደለሁም ብለው ሊገልጹ ይችላሉ እንጂ የፓርቲው ውሳኔ አይደለም ብለዋል፡፡

አሐዱም ፓርቲው አሁን ያለበት ሁኔታ ምንድነው ሲል የጠየቀ ሲሆን አቶ ቀጀላ የምርጫ ቅስቀሳ ከማካሄድ በፊት ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድ አስፈላጊ በመሆኑ ጉባኤውን ለማካሄድ ሂደት ላይ መሆናቻውን ተናረዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ በርካታ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ ግብራቸውን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ መጀመራቸው ይታወሳል አሐዱ ራዲዮ 943

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *