እስራኤል ግብጽ ከሃማስ ጋር ታሸማግላት ዘንድ ጠይቃለች
By: Date: February 22, 2021 Categories: ዜና

እስራኤል የግብፅን ምልጃ የጠየቀችው የእስረኛ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡እንደ አል-አረቢያ ዘገባ ግብፅ በእስራኤልና በሃማስ መካከል በቅርቡ በተደረገው ውይይት ማማለዷን ነው የገለፀው፡፡

በዚያም መሰረት እስራኤል የያዘቻቸውን የሃማስ ኃይሎች ለቡድኑ ለመመለስ መልካም ፈቃድ ይኖራት ዘንድ አግባብታታለች ነው ያለው ዘገባው፡፡ሃማስ በበኩሉ እስራኤል በእስር ቤቶቿ ያጎረቻቸውን በርካታ ቁጥር ያላቸውን ፍልስጤማውያንን ትፈታ ዘንድ በተደጋጋሚ መጠየቁ ይታወቃል፡፡

ሃማስ ከዚያም ውጪ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የዓሳ ማስገር ስራቸውን እንዳታስተጓጉል ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ባለፈው ታህሳስ ወር እስራኤል በሃማስ የታገቱባትን ሁለት ዜጎቿን ለማስለቀቅ በሚል የኮሮና ቫይረስን ክትባት በጋዛ ሰርጥ ለማዳረስ ሃሳብ ማቅረቧና ሃማስም የእስራኤልን ሃሳብ ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል ሲል ዘገበው አሩትዝ ሼቫ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *