አዲስ አበባ ትምሕርት ቤት ውስጥ በኮቪድ 19 በሽታ የተያዙ ተማሪዎች እየተገኙ ነው
By: Date: February 22, 2021 Categories: ዜና Tags:

በራስ አምባ ትምህርት ቤት በኮቪድ 19 ያለባቸዉ አራት ተማሪዎች በመገኘታቸዉ በየክፍሉ ምርመራ መደረግ መጀመሩን የትምህርት ቤቱ ርእሰ መመህር አቶ ስንታየዉ ገለታ ለአሀዱ ተናግረዋል፡ አሁን ናሙና ከተወሰደላቸዉ 22 ተማሪዎች በተጨማሪ በሁለተኛዉ ዙር በነገዉ እለት ማክሰኞ ከሶስት ክፍሎች ናሙና እንደሚወሰድ አስታዉቀዋል፡፡

አራቱ ተማሪዎች ኮቪድ እንዳለባቸዉ የታወቀዉ ቤተሰቦቻቸዉ ናሙና ሰጥተዉ ነዉ ተብሏል፡፡ተማሪዎቹ ከየክፍሉ አንድ አንድ 4 በመሆናቸዉ ከሁሉም ክፍሎች ናሙና ይወሰዳል ብለዋል፡፡

የመማር ማሰተማር ሂደቱ አሁንም ቀጥሏል ያሉ ሲሆን ለመምህራን ናሙና ለመዉሰድ ታስቧል ወይ የሚለዉን አሀዱ የጠየቀ ቢሆንም ምልክት ከታየ እንደሚወሰድ እና አሁን ላይ ከተማሪዎች ብቻ ለመዉሰድ መታቀዱን አቶ ስንታየዉ ነግረዉናል፡፡

በራስ አምባ ትምህርት ቤት መመህር የሆኑ ግለሰብ ለአሀዱ እንደተናገሩት ደግሞ በትምህርት ቤቱ እስካሁን 6 ተማሪዎች ኮቪድ ተገኝቶባቸዋልየታወቀዉም በጠና ስለታመሙ ነዉ ብለዋል፡፡

የሚያዙ ተማሪዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በትምህርት ቤቱ አሁን እየተደረገ ያለዉ የምርመራ ቁጥር በቂ አይደለምና ትኩረት ያስፈልጋል ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ አሐዱ ራዲዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *