ሱዳናዊ ባለሀብት በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊያለሙ ነው

ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ልታለማ ነው። በሰሜን ምስራቅ ሱዳን ኑቢያ በርሃ እጅግ ሰፊ በርሃማን ስፍራ ዳል ግሩፕ የተሰኘ ድርጅት በመስኖ ለማልማት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ፋይናሻል ታይምስ ዘግቧል።

የዳል ግሩፕ ሊቀመንበር ኦስማን ዳውድ እንደሚታወቀው አካባቢው በርሃ ነው ነግር ግን አረንጓዴነት በመቀየር ላይ እንገኛለን ብለዋል። የአባይ ወንዝ አለን፣ ሌሎች በርካታ ወንዞች አሉን ፣ የዝናብ ውሃ በተመሳሳይ አለን ያሉት ሊቀመንበርሩ በዓለም ላይ ሜዳማ ሀገር አለን ብለዋል።

አቡ ሃማድ በተሰኘው የሱዳን አካባቢ በ225 ሚሊየን ዶላር ወጪ ድርጅቱ ከዱባዩ ሮያል ግሩፕ ጋር በጋራ በመሆን የመስኖ ልማቱን እንደሚሰራ ተነግሯል። ከአባይ ወንዝ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ለሚለማው እርሻ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት ከአባይ ወንዝ ውሃ እንደሚሳብ ነው። ፋና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *