ለትግራይ ክልል 71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና ግብዐቶች ተልከዋል

በትግራይ ክልል ለደረሰው አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እስካሁን ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና ግብዐቶችን በክልሉ ለሚገኙ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ማዕከላት በመላክ ለሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

ለደረሰው አስቸኳይ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች የያዘ ቡድን ወደ ትግራይ መላኩን ጠቅሷል። ሚኒስቴሩ፣ ተጠሪ ኤጀንሲዎቹ እና የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከሰብዓዊና ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ድጋፍ እና መልሶ ማቋቋም ላይ በስፋት እየሰሩ እንደሚገኙም በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል።

“በተጎዱ አካባቢዎች ያለው የህብረተሰብ ጤና እና ደህንነት ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ሲሆን መንግስት በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች የድንገተኛ ምላሽ እየሰጠና ወገኖች ወሳኝ የጤና አገልግሎቶች እንዲያገኙ ለማድረግ ላለፉት በርካታ ሳምንታት እየሰራ ይገኛል” ሲል ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *