የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል 18.3 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አድርጓል

ድጋፉን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብረሃም በላይ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ አስረክበዋል።ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ድጋፉ በጁንታው እኩይ ተግባር ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ የትግራይ ወገኖች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ነው።

የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዲሞክራሲ ህይወቱን የሰዋ ህዝብ በመሆኑ በነሱ የደረሰው ጉዳት የኛም ጉዳት ነው፤ በቀጣይ ክልሉን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን የድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *