“የሱዳን ጦር ከጥቅምት 6 ጀምሮ ከገባበት መሬት ለቆ እንዲወጣ” ኢትዮጵያ ጠየቀች
By: Date: January 21, 2021 Categories: ዜና Tags:

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሱዳን ጦር ከጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ከገባበት የኢትዮጵያ መሬት በሙሉ ለቆ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ላለው የድንበር ድርድር ጥሪ እንደምታደርግና ነገርግን ከድርድሩ በፊት የሱዳን ጦር ወደ ቦታው ተመልሶ አካባቢው ሰላማዊ ሲሆን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የድንበሩ ጉዳይ ከህዳሴው ግድብ ጋር አይገናኝም ያሉት ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የተስማማችው በድንበር አካባቢ ጸረ-ሰላም ሀይሎች እንዳይንቀሳቀሱ እንጂ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲገቡ አልነበረም ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ይሄን ያሉት ሰሞኑን የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክርቤት ፕሬዘዳንት አልቡርሃን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ወታደር ለማሰማራት ተስማምተናል ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

አምባሳደር ዲና ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ጥሳ እንድትገባ የሚፈቅድ አመራር የለም፤ከሱዳን አመራር የሚመጣው መግለጫ “ስህተት” ነው ብለዋል፡፡ ድንበሩን በሚመለከት የኢትዮጵያ መንግስት አቋም ድርድር ለማድረግ የሱዳን ጦር ለቆ መውጣት አለበት ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ጸረ-ሰላም ሃይሎችን ለከላከል መስማማት ማለት የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ መስማማት ማለት አይደለም ያሉት አምበሳደሩ ሱዳን ከጃርባችን ትወጋናለች ብለን አልጠበቅንም ነበር፣ እንደምንየው ከሆነ አቋሟ የሱዳንን ህዝብ አይወክልም ብለዋል፡፡

አምባሳደር ዲና ኢትዮጵያ በሱዳን ሰላምና መረጋጋረት ለማምጣት ሰርታለች በቅርቡ እንኳን በሽግግር ወቅት ሚና ነበርት ብለዋል፡፡ በድንበሩ ጉዳይ ለማደራደር የሚጥሩት ሀይሎች እናደንቃለን ነገርግን ሌላ ወገን አያስፈልግም ሱዳም ጦሯን ካስወጣች ሁለቱ ሀገራት ቁጭ ብለው መደራደር ይችላሉ ብለዋል፡፡

የህዳሴው ግድብ ሙሌት ከ ድርድሩ ሂደት ጋር ስላለመያያዙ አምባሳደር ዲና የግድቡ ሙሌት ጉዳይ ከድርድሩ ሂደት ጋር እንደማይገናኝ ተናግረዋል፡፡ የግድቡ ድርድር የሚያያዘው ከግንባታው ሂደት ጋር መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር ሲና እንደገለጹት በግድቡ ዙሪያ የሱዳን ጥቅም ተጠብቆላታል ብለዋል፡፡ጋር መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር ዲናእንደገለጹት በግድቡ ዙሪያ የሱዳን ጥቅም ተጠብቆላታል ብለዋል፡፡ የድንበሩ ጉዳይም እንዲሁ ከህዳሴው ግድብ ጋር እንደማይገናኝ አምባሳደር ዲና ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *