አክቲቪስት ናትናኤል መኮንን ገዢው ፓርቲ በውስጥና ከሀገር ውጪ ገንዘብ የሚከፍላቸውን አክቲቪስቶች አጋልጣለሁ አለ
By: Date: January 21, 2021 Categories: ዜና

ብልጽግና ፓርቲ ከውጭ ሀገር የሚገቡ አክቲቪስት ነኝ ባይን እየሰበሰበ ሆቴል እየያዘ ብር መክፈሉን ካላቆመ ፓርቲው በፍጹም ወደፊት ሊራመድና ሊለወጥ አይችልም:: ከፋይም ተከፋይም ሆዳም ሆኖ የህዝብን እሮሮ መስማት አይቻልም:: ይህ ነገር በጥቂት ሰዎች እንደሚፈፀም አውቃለሁ እንደው ጥሩ ነገር እንኳን ሰርተውና አድርገው ቢሆን ይሁን ይባላል አንድም ነገር ሳይሰሩ ሀገራቸውን ሳይጠቅሙ በወሬ ብቻ የህዝብን ብር ለእንዲህ አይነቱ ወጣት ጡረተኛ ሆቴል እየያዙ ገንዘብ መክፈል ነውር ነው::

ይህ ክፍያ የተባለ ነገር ሀገር ቤት ውስጥ ላሉትም እንዳለ እውቃለሁ አስፈላጊ ከሆነ ከሀገር ቤት እስከ ውጪ ድረስ ያሉትን ስም ዝርዝራቸውንና የብሩን መጠን መናገር ይቻላል:: በበኩሌ ይህን ጉዳይ ከአንድም ሁለት ባለስልጣኖች በስልክም በአካልም በማግኘት መቆም እንዳለበት አሳውቂያለሁ:: ሌላውን ጉድይ በዝርዝር እመለስበታለሁ፡፡ (ናትናኤል መኮንን)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *