ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ የትምህርት ዞን ተብሎ ሊሰየም ነው

ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ የትምህርት ዞን እንዲሆን መወሰኑ ይደርስ የነበረውን እንግልት በማስቀረት ትክክለኛ የተቋም መረጃን በአንድ ስፍራ ለማግኘት እንደሚያስችል ተገለጸ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ ለአሀዱ እንደተናገሩት በትምህርት ዘርፉ የተበጣጠሱ የአገልግሎት ሴክተሮችን ወደ አንድ ለማምጣት ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮሜዳ ባለዉ አካባቢ የትምህርት ዞን ብሎ በመሰየም በትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ዉስጥ ተቋማቱ አገልግሎት እንዲሰጡ ሊደረግ ነው። የተገልጋይን እንግልት ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

በኤጀንሲዉ ዉስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚደረጉት እነዚህ ተቋማት የትምህርት ጥራት ተጠያቂነትና ተደራሽነት እንዲሁም ስለ ትምህርት ተቋማት ትክክለኛ እና የተሟላ አገልግሎት እንዲገኝ በማድረግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸዉ። አሐዱ ሬዲዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *