በሱዳን የሟቾች ቁጥር 155 ደረሰ
By: Date: January 20, 2021 Categories: ዜና

በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 155 ደረሰ፡፡ በዳርፉር የተቀሰቀሰውን ደም አፍሳሽ ግጭት ተከትሎ የሱዳን ጦር በአካባቢው የተሰማራ ሲሆን ከተገደሉት 156 ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች ክፉኛ ቆስለዋል። ባሳለፍነው ቅዳሜ በአረብ ዘላኖች እና አረብ አይደለንም በሚሉት የማሳሊት ጎሳ አባላት መካከል በምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት መዲና ኢል ገኒና ግጭት መቀስቀሱን የግዛቲቱ ገዢ ሞሃመድ አል ዶዩማ ተናግረዋል።

50 ሺ ያህል ዜጎች ግጭቱ ለስደት መዳረጉን ዓለም አቀፋዊው የረድኤት ድርጅት የልጆች አድን(Save The Children) አስታውቋል። ከካርቱም እና ከሌሎች ግዛት የተውጣጡ የፀጥታ አካላት ወደ ምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት ያቀኑ ሲሆን በግዛቲቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *