የመንግስታቱ ድርጅትን ሽፋን በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ የነበሩ 30 ሺህ ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር እና ጌጣጌጦች ተያዙ
By: Date: January 18, 2021 Categories: ዜና

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠርያ ጣብያ ኃላፊ አቶ ዋርዮ ጉዮ እንደገለፁት በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 2 ሰዓት የህዝብ ጥቆማ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።

በጥቆማው መሰረትም የተያዘው ተሽከርካሪ ፍተሻ ሲደረግበት 30 ሺህ ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር እና 100 ኪሎ ግራም የብር ጌጣጌጦች በመንግስታቱ ድርጅት እና በዓለም ህጻናት ድርጅት ፈንድ ቀረጥ ተከፍሎባቸው የገቡ ቁሳቁሶችን ሽፋን በማድረግ በኮድ ቁጥር 3 አዲስ አበባ በሰሌዳ ቁጥር 193006 ወደ አዲስ አበባ ሲገባ መያዙን ሀላፊው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡

ጥቆማውን በመቀበል ፍተሻ ያደረጉት የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ፌድራል ፖሊስ ዲቪዥን ሀይል 4 እንደሆነም ተገልጿል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር አይናለም ግርማ እንደገለፁት የወረዳው ማህበረሰብ ህገወጥነትን ለመከላከል በርካታ ስራዋችን ከፅ/ቤቱ ጋር እየሰሩ መሆኑን

አሳውቀው የዛሬውም ጥቆማ ከማህበረሰቡ ጋር የመስራት ውጤት መሆኑን ገልፀዋል። ኤትዮ ኤፍ ኤም ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ ሁለት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት እንዳገኘው መረጃ ከሆነ በአካባቢው ተጨማሪ እና የተጠናከረ ፍተሻ ይደረጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *