የጥምቀት በዓልን በጎንደር ለማክበር የሀገር ውስጥ እና የውጭ እንግዶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው።
By: Date: January 16, 2021 Categories: ዜና Tags:

የጥምቀት በዓልን በጎንደር ለማክበር የሀገር ውስጥ እና የውጭ እንግዶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው። የጎንደር ነዋሪዎችም እንግዶቻቸውን መቀበል ጀምረዋል፡፡ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ማስታወቁን አብመድ ዘግቧል።

የተለያዩ የወጣት አደረጃጀቶች እና የሲቪክ ማህበራት እንግዶች ተደስተውና የሰላም ችግር ሳይገጥማቸው በዓሉን እዲያሳልፉ ለማድረግ ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ እየሠሩ ነው ተብሏል። በተጨማሪም የጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ ሥፍራው የሚያቀኑ እንግዶችን በአግባቡ ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አስታወቀ። በአማራ ክልልየጥምቀት በዓል ደምቆ ከሚከበርባቸው አካባቢዎች መካከል ምንጃር ሸንኮራ አንዱ ነው።

በዓለ ጥምቀቱ በወረዳው በሚገኝ የሸንኮራ ወንዝ 44 ታቦታት አንድ ላይ በተሰባሰቡበት ይከበራል። 44ቱ ታቦታት እስከ 18 ኪሎ ሜትር ድረስ ተጉዘው ነው በጥምቀተ ባህሩ የታቦታት ማደሪያ የሚሰባሰቡት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *