የግእዝ መምህሩ በሲያትል

በጆርጅ ዋሽንግተን ዩንቨርስቲ የምስራቅ አፍሪካና የአረብኛ ቋንቋዎች መምህር የሆነው አሜሪካዊው ሀምዛ ዛፈር በሲያትል ከተማ ላለፉት ሁለት ዓመታት በግሉ ከ200 በላይ ተማሪዎችን የግእዝ ቋንቋ አስተምሯል።

መምህሩ ቋንቋውን ማስተማር በግሉ የዛሬ ሁለት ዓመት ሲጀምር ትምህርቱን የሚፈልግ ሰው አይኖርብ ብሎ ቢያስብም በቀናት ውስጥ ከ30 ያላነሱ ተማሪዎች ተመዝግበው ክፍሉን ሞልተውት መመልከቱ ቋንቋውን በግል ማስተማሩን እንዲገፋበት እንዳበረታታው ይገልፃል፡፡

የግእዝ ቋንቋን ከተቋም ውጭ አንድ የውጭ ተወላጅ በግሉ ትምህርት ቤት ከፍቶ ሲያስተምር ሀምዛን የመጀመሪያው ያደርገዋል። በግዕዝ ቋንቋ በርካታ ጥንታዊ የሥነ፡ፅሁፍ፣ የፍልስፍና፤ የሥነ ክዋክብት እንዲሁም የሕክምና ፅሁፎች በመኖራቸዉ ቋንቋዉን ማጥናት የመካከለኛዉ ዘመንን የአፍሪካ ስልጣኔና ታሪክ ላይ ለሚደረገዉ ምርምር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላለው ሀምዛ ቋንቋዉን እንዳጠና ይናገራል።

ከሴሜቲክ ቋንቋ የሚመደበዉ የግዕዝ ቋንቋ በአክሱም ዘመነ መንግስት ይነገር እንደነበር መዛግብት ይጠቁማሉ ። በግዕዝ የተፃፉ አበዛኛወቹ መፃህፍት ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸዉ ሆኑም የመካከለኛዉ ዘመን ስልጣኔን የሚሳያሳዩ የተለያዩ የስነፅሁፍ፣ የፍልስፍና፤ የህክምናና የስነ ከዋክብት መፃህፍትም በዚሁ ቋንቋ እንደሚገኙ የዘርፉ ተመራማሪወች ይገልፃሉ።

በጀርመን ሃገር የሚገኘው የሃምቡርግ ዩንቨርሲቲ እና የካናዳው ቶሮንቶ ዩንቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ዉጭ የግዕዝ ቋንቋን የሚያስተምሩ ብቸኛ ተቋማት ናቸው። የቻይናው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲም በቅርቡ የግዕዝ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምር አስታውቋል። ምንጭ አድማስ ራዲዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *