የአውሮጳ ሕብረት ለኢትዮጵያ በጀት መደጎሚያ የሚሰጠውን የ88 ሚሊየን ዮሮ ድጎማ ማቋረጡ

የአውሮጳ ሕብረት የሰብዓዊ ርዳታ ድርጅቶች ወደ ትግራይ ክልል መግባት እስካልቻሉ ድረስ ለኢትዮጵያ በጀት መደጎሚያ የሚሰጠውን የ88 ሚሊየን ዮሮ ድጎማ ማቋረጡን ሮይተርስ ዘገበ።

የሕብረቱ የውጪ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በበይነመረብ ባሰራጩት መልዕክት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትግራይ ውስጥ ያለውን ግጭት በማስቆም አምና የተቀበሉትን የሰላም ኖቤል ሽልማት መርሕን የሚያረጋግጥ ተግባር እንዲፈጽሙ መጠየቃቸውንም የሮተርስ ዘገባ ጠቅሷል።

ቦሬል አክለውም፣ «ለመርዳት ዝግጁነን ሆኖም የሰብአዊ ርዳታ ድርጅቶች መንቀሳቀስ ካልቻሉ የአውሮጳ ሕብረት ለኢትዮጵያ መንግሥት ለመስጠት ያቀደውን የበጀት ድጋፍ ለመልቀቅ አይችልም» ማለታቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል። በጉዳዩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጽሕፈት ቤት አስተያየት ለማካተት አለመቻሉንም ሮይተርስ አመልክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *