የመተከል ፍርድ ቤት ዳኛ

ከአስር ዓመታት በፊት፣ ደሴ ቢዝነስና ሥራ አመራር ኮሌጅ (ኋላ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ) 99 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተወላጅ የሆኑ (የበርታ፣ የጉምዝ፣የሺናሻ፣የማኦና ኮሞ ብሔረሰቦች) ተማሪዎችን ለሦስት ዓመታት የሕግ ትምሕርት አስተምሬያለሁ። ከሁሉም ተማሪዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበረኝ። አሁንም ቢሆን ቢያንስ ከተወሰኑት ጋር በተለያዩ መንገዶች እንገናኛለን። አሶሳ በሔድኩበት ወቅትም የተለያዩ ስጦታዎችን ያበረከቱልኝም አሉ።

ይሁን እንጂ፣ ከተማሪዎቼ መካከል መተክል ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ የሚደግፉ (የሚያስተባብሩ)የጉምዝ ተወላጆች መኖራቸውን ስሰማ በጣም አዘንኩ።
ካስተማርኳቸው መካከል አንዱ (ጨበሌ ያደታ) በዚሁ ድርጊት በመሠማራቱ ከታሠረ ሁለት ዓመታት ሊሆነው እንደሆነ ሰማሁ።

ሌላኛው ተማሪዬ፣ ደርጉ ድንኳን (ፎቶው የተለጠፈው) ደግሞ፣ የመተክል ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሬጂስትራር ሆኖ እየሠራ “ቀያዮቹን” በማስገደልና በማስተባበር ድርጊት ተጠርጥሮ በዛሬው ዕለት (ጥር 6) ጧት ላይ (4፡00 ገደማ) ፖሊስ በቁጥጥር ሊያውለው ወደ ቤቱ ሲሔድ ወደ ፌደራል ፖሊሶች ተኩስ በመክፈት አንድ ፖሊስ ካቆሰለ በኋላ በፖሊስ እርምጃ እንደተወሰደበት ሰማሁ።

ከአስተማሪና ተማሪ ግንኙነትም ባለፈም እንደ ወንድም ስንረዳዳ የነበሩ ተማሪዎቼ፣ የሕግ ባለሙያዎቹ፣ የእኔኑ ዘመዶች (ሕጻናት ሳይሉ ሴቶች) ያለምንም ምክንያት፣ ከሚገድሉት ውስጥ አብረው ማበራቸውን ስሰማ ሀዘኔ በረታ! (ውብሸት ሙላት)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *