በዋሻ ውስጥ የተከበቡ ቀሪ የጁንታው መሪዎች 48 ሰኣት ገደብ ተሰጣቸው

በየዋሻው የተደበቁ የጁንታው ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋደል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጥሪ አቅርበዋል። “ትርጉም ለሌለው ጁንታ ጠባቂ በመሆን ውድ ህይወታቸውን አትገብሩ፣ ከቻላችሁ ይዛችኋቸው፣ ካልቻላችሁ በሰላም ለሰራዊቱ እጅ እንድትሰጡ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ጁንታው ተመልሶ ይመጣል በሚል ያላቸው ግምት የተሳሳተና የጁንታው ቡድን ዘመን ያከተመ መሆኑን አውቀው፣ ከሀገራቸውና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ ሽግግር መንግስት ጎን በመሆን ትግራይን እንዲያደራጁ፣ እንዲያለሙና መላው ህዝብም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የጁንታው ቡድን አመራሮች ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ በመቀሌ በተካሄደው ዘመቻና ድምሰሳ ወቅት በ48 ሰዓት እጅ እንዲሰጡ ቢለመኑም፣ በማናለብኝነትና ትዕቢተኝነት እምቢ በማለት ወደ ጫካ መግባታቸውን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አስታውሰዋል።

በድጋሚም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገር ሽማግሌ ጭምር በመላክ እጅ እንዲሰጡ፣ ትጥቅ እንዲፈቱና ጉዳዩቸው በህግ እንዲታይ ቢያስጠይቅም አሻፈረኝ ብለውና የያዙትን የጥበቃ ሀይል በመተማመን እንዲሁም “ተመልሰን እንነሳለን” በሚል የድሮ ብሂል ተሳስተው ያለ እድሜያቸው በዱር በገደሉ ተሸሽገዋል ብለዋል። ዋሻዎችን በመጠቀምም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን እይታ ውጪ ለመሆን ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ሲሉም ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *