በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ስራ ጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ቦሌ ፣ ስታዲየምና አካባቢው የውሃ እጥረት አጋጥሟል!

በመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ስራ በጥንቃቄ ጉድለት ባጋጠመ ችግር ፣ 700 ሚሊ ሜትር ስፋት ያለው የውሃ መስመር ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ስራውን እየከወነ የሚገኘውና ጉዳቱን ያደረሰው CCCC የተባለ ተቋራጭ ስለመሆኑም ብስራት ራዲዮ ሰምቷል፡፡ በግንባታ ስራው ሂደት ለውሃ መስመሩ ጥንቃቄ ባለመደረጉ ፣ ውሃ በሚያስተላልፈው ከባድ መስመር ላይ ጉዳቱ ሊደርስ ችሏል፡፡

በዚህም ምክንያት በጋንዲ ሆስፒታል አምባሳደር አካባቢ፣ ቦሌ ሮድ እስከ ደንበል በአጠቃላይ በስታዲየም ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት መቋረጡ ተገልጿል፡፡ መስመሩን ጠግኖ ወደ መደበኛ ስርጭት ለማስገባት የተለያዩ ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸዉ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *