ከዛሬ 86 አመት በፊት በ1927 እትዮጵያ ውስጥ አውሮፕላን ይመረት ነበር።
By: Date: January 9, 2021 Categories: ታሪክ Tags:

አሁን ያለው የእትዮጵያ አየር መንገድ እንኳን ሊቋቋም ገና ሳይታሰብ በፊት በአፄ ኃይለስላሴ የተቋቋመ የአውሮፕላን ማምረቻ በ1927 ተከፍቶ አውሮፕላን ማምረት ጀምሮ የመጀመሪያዋ አውሮፕላን ስሟ ኢትዮጵያ 1 ወይም ፀሀይ በመባል ተሰይማ ነበር። ይህች አፍሪካ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራችው፡፡

አውሮፕላን የክንፎቿ አብዛኛው ክፍል ከእንጨት የተሰራ ሲሆን 115 የፈረስ ጉልበት ነበራት። በ1927 በእትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የአውሮፕላን ምርት ተጀምሮ እስከ 1928 ድረስ በአመት ሶስት አውሮፕላኖችን የማምረት ውጥን የተያዘ ቢሆንም በ1928 ኢጣሊያ ወረራ እስክትጀምር ድረስ አንድ ያለቀላት አውሮፕላን ተሰርታ አካሏ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ተቀብታ ፀሐይ ተብላ ተሰይማ ነበር።

ይህች የመጀመሪያዋ አውሮፕላን የመጀመሪያውን በረራዋን በ1928 ታህሳስ ወር ላይ በአዲስ አበባ ያደረገች ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ እስከ 6100 ሜትር መብረር የምትችልና በሰዓት ከ150 እስከ 185ኪሎ ሜትር መብረር የምትችል 115 የፈረስ ጉልበት ካለው ሞተር የተሰራች 7 ነጥብ 32 ሜትር ርዝመትና ሁለት ሰው መያዝ የምትችል ለ30 ሰአት የበረረች አውሮፕላን ነበረች።

ጣሊያኖች አትዮጵያ ከገቡ በኋላ የአፄው የግል ፓይለት ሉዲግ ዌበር ላይ ጭምር ከፍተኛ ጫና በማሳደር ስራውን በማስተጓጎል ፀሐይ ቆማ ከነበረችበት ጃንሜዳ በማስነሳት በአዲስ አበባ ኣካባቢ ካበረሯት በኋላ ወደሀገራቸው ወስደው በኢጣሊያን አቪየሽን ሙዚየም ውስጥ የንጉስ እውሮፕላን በመባል እሰከዛሬም ትጎበኛለች። (ሜታትሮን)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *