ከኬኒያ የስደተኞች ካምፕ እስከ አሜሪካ የምክር ቤት አባልነት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኦባላ

የታዳጊነት እድሜውን በስደተኛ ካምፕ ውስጥ አሳለፈ፡፡ የዛሬ 5አመት እንኳን በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ኦባላ ይፀልያል ያልማል፡፡ መልካም ህይወትን ለመኖር ያቅዳል ይመኛል:: ተስፋ መቁረጥ በእርሱ ዘንድ የለም፡፡

ከዚያም ከኬንያ የስደተኞች ካምፕ ወደ አሜሪካ የመሄድ እድል ገጠመው:: ቀጥሎም የአሜሪካ ዜግነት ተቀበለ:: ይህን ሁሉ የስደት ህይወት አሳልፎ እነሆ በዚህ ዓመት ያለፈው ሰኞ በአሜሪካ ሜኒሶታ ግዛት ውስጥ የኦስቲን ከተማ ምክር ቤት አባል ሆኖ ቃለመሃላ ፈፅሞ የመቀመጫ ወንበሩን ተረከበ፡፡

ይህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ኦባላ ኦጅሉ ኦባላ እንኳን ደስ አለህ በርታ እንላለን፡፡ በህይወት ጎዳና ፅናት እና አወንታዊ አስተሳሰብ ለስኬት ወሳኝ ናቸው:: ሁላችንም በያለንበት የህይወት መስክ እንበርታ እንፅና ተስፋ ሳንቆርጥ እስከመጨረሻው እንትጋ፡፡ ከፈጣሪ ጋር ስኬት የእኛ ይሆናል፡፡ በደጀኔ አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *