ይድረስ ለታምራት ላይኔ የቁና ገብስና የስኒ ቅቤ ነጻሪ (ፕሮፌሰር ምንዳርያለው ዘውዴ)

ለትውስታዎ እንዲረዳዎ አንደኛ በጭራቁ መለስ ትእዛዝና በገነት እሽክም እሽቅንጥ ባይነት 40ዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ስንባረር እርስዎ ውሳኔው ተገቢ መሆኑን ለህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በእርሶ የሚመራ ብሄራዊ ኮሚቴ አቊዋቁመው በደምፍላት በየሚዲያው ሲያስወግዙን ነበር።

ሁለተኛ በበደኖ በኢንቁፍቱ በአርባጉጉ አማራው በዘር ተለይቶ ሲጨፈጨፍ እርሶ ልብዎ በደስታ ከመጋሉ ብዛት አላስችል ብልዎት አሰላ መጡ። ህዝቡም ከወልኬሳ ወንዝ እስከ አረንጉዋዴው ስታዲየም ድረስ በፈረስ አጅቦ ተቀበለዎ።ስታዲየም ደርሰው ያደረጉት ንግግር እንዲህ ይላል። “ነፍጠኞች እዚህ ምን ሊያደርጉ መጡ? እናንተን ሊጨቁኑ ሊገዙ ሊረግጡ ነው። እና ነፍጠኛ ዛሬስ እዚህ ምን ይሰራል?” ወዘተ የሚል ቀጥተኛ የጄኖሳይድ ቅስቀሳ ነበር።

ሶስተኛ በአማራው ላይ እየደረሰ የነበረውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ቢቻል ለማስቆም ባይቻል ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳ ወቅ ፕሮፌሰር አስራት ወደድሬዳዋ ሲሄዱ የሶማሌ ህዝብ በታላቅ ሰልፍ ከአውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ በማጀብ ደማቅ አቀባበል አደረገላቸው። ያነዜ ኒኦፋሺስታዊ የቀወተ አንደበትዎን በላላዎትና ወደድሬ ሄዱ። እዛም እንደደረሱ። “አማራን ለምን ትደግፋላችሁ? እኛን የህዝብ ልጆች አባከና ሳትሉ፣ ፕሮፌሰር አስራትን እንደምን በክብርና በፍቅር ትቀበላላችሁ? ነፍጠኞች እኮ እናንተን እንትን ለባሽ እንትን እንትን እያሉ ሲጠሩዋችሁ አልነበረም?” የሚል በስድብ የታጀለ ሰይጣናዊ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ አደረጉ።

አራተኝም የትህነግ አሽከር የነበረውን ኢህዲንን ብአዴን የሚል አዲስ ከፈን ጌታው ትህነግ ያሰፋለት መሆኑን አስመልክታችሁ በባህርዳር ዳንኪራ ስትረግጡ አንድ ታዳሚ “አማራው በምስራቅ በመሀል እና በደቡባዊ ኢትዮጵያ ሲጨፈጨፍ እኛ ምን ሰራንለት?” ብሎ ሲጠይቅ “አማራው እዛ ለምን ሄደ? ሊጨቁንና ሊበዘብዝ ነው። እና ለአንተ እዚህ ላለኸው አማራ አንድ ቁና ገብስ እና አንድ ስኒ ቅቤ ልኮልሀል። አሁን ደርሶ ለእሱ የምትከራከርለት?” በማለት መለስ ያጎረብዎትን ኒኦፋሺስትነት ሲያስታውኩ ዋሉ። የአማራውን በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ተዘዋውሮና ሰርቶ የመኖር ተፈጥሯዊ ህጋዊና ታሪካዊ መብት የሚገፍ ፋሺስታዊ መርዝ ተከሉ።

አምስተኛ መተከል ወደቤጉ እንዲከለል የአውራጃውን ህዝብ ወኪሎች በፓዊ ሰብስበው መርዛማ ሰበካ ቢያደርጉም ተሰብሳቢው እምቢ አለ። ሳይወድ በግዱ ለማሳመን ከታደሰ ካሳ ጥንቅሹ ጋር ለሶስት ወር የማያባራ ስብሰባና ዛቻ እስርና ድብደባ በአማራውና በአገው ህዝብ ላይ አደረሱ። ህዝቡ እንዲህም ሆኖ “እኛ ጎጃሞች ነንና መከለል ያለብን ወደአማራ ነው” ብሎ ቢል ከፊሉን አሳስረው ከፊሉን አስገርፈው በራስዎ ግዜ መተከል ወደቤጉ እንደከለል አደረጉ። እናም ዛሬ በየቀኑ ለሚታረደው አማራና አገው የመጀመሪያውን ኒኦፋሺስታዊ የመሰረት ድንጋይ ጣሉ።

ይህንን ሁሉ የፈጸሙት በእንዱቅዱቅ ካድሬነትዎ፣ በትህነግ አሳፋሪ አሽከርነትዎ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስት ርነትዎ በሰጠዎ ትልቅ ሀገራዊ ስልጣን ጭምር ነው።

ቢያንስ ቢያንስ የኢትዮጵያን ህዝብ ባጠቃላይ የአማራንና የአገውን ህዝብ በተለይ፣ ይቅርታ በይፋ ሊጠይቁ ይገባል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *