በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተከሰተው ምንድን ነው?

በርካታ የፌስቡክ ገፆች እና የትዊተር አካውንቶች በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ጦርነት እየተካሄደ እንደሆነ በመግለፅ እና ይህን ያስረዳሉ ያሏቸውን ፎቶዎች እና ቪድዮዎች በማጋራት ላይ ይገኛሉ። ሁሉንም መረጃዎች አንድ በአንድ ማጣራት ባንችልም ያገኘናቸው የተጣሩ መረጃዎች ይህን ይመስላሉ።

እሁድ እለት ሱዳንን ከኢትዮጵያ በሚያዋስነው የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በሱዳን ጦር እና በአካባቢው ሚሊሻ መካከል ግጭት እንደነበር አንድ የወረዳው ከፍተኛ ባለስልጣን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል፣ ሰኞ እለትም የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ጨምረው ገልጸዋል። በዚህም በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ሰላም በር በተባለች ቀበሌ የሱዳን ጦር ጥቃት ማካሄዱን፣ የአርሶ አደሮች ሰብልና መሳሪያ ላይ ጉዳት መድረሱን እንዲሁም የሰው ጉዳት መከሰቱን በስፍራው ካሉ ምን ጮች አረጋግጠናል።

ሌላው ግጭት ተከሰተበት የተባለው ስፍራ የመተማ ወረዳ ነበር። የመተማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አየለ ግርማ እንዲሁም አንድ የአካባቢው ነዋሪ በወረዳው ምንም አይነት ግጭት እንዳልተፈጠረ ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቀዋል። ነገር ግን የመተማ አዋሳኝ በሆነችው ምድረገነት ከተማ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

በቅርቡ በሱዳን በተካሄደው 2ኛው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር የጋራ ከፍተኛ የፖለቲካ ኮሚቴ ውይይት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጥቅ ምት 30 ጀምሮ የሱዳን ወታደራዊ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ በተደራጀ መልኩ ጥቃት እየፈጸሙ ስለመሆናቸው አንስተዋል፡፡

በዚህም “የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የግብርና ምርቶች ተዘርፈዋል፣ ካምፖቻቸው ወድመዋል እንዲሁም የራሳቸውን የእርሻ ምርት እንዳያጭዱ ተደርገዋል” ያሉት አቶ ደመቀ በርካታ ንጹሀን ስለመገደላቸው እና ስለመቁሰላቸውም ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *