
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ኀዳር 21/2013 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ኹለተኛ ልዩ ስብሰባውን የሚያካሂድ ሲሆን በስብሰባው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ይገኛሉ።
ከምክር ቤቱ አባላትም በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለሚያነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎም ይጠበቃል።በስብሰባው ላይ የሐይማኖት አባቶች በአዲስ አበባ የሚገኙ አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚገኙ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።