የጡረታ ደመወዜን ይዘው ሲያስፈራሩኝ ለዘመቻ ወጣሁ-አዛውንቱ ሚሊሻ
By: Date: November 26, 2020 Categories: ፖለቲካ

ሕወሓት ጁንታ አመራሮች የአስም በሽተኛ ሆኜ፤ የልብ ቀዶ ህክምናም አድርጌ እንኳን ሳይራሩ የጡረታ ደመወዜን ይዘው ሲያስፈራሩኝ ለዘመቻ ወጣሁ-አዛውንቱ ሚሊሻ
አቶ መብራቱ ታደለ የ62 ዓመት አዛውንት ናቸው፤ ስድስት ሴት ልጆችን ወልደው ስመዋል። የልጅ ልጆችን አፍርተውም አያት ሆነዋል።

አዛውንቱ የአስም ህመምተኛ ናቸው። የጤናቸው እክል አስም ብቻ እንዳልሆነና በቅርቡም የልብ ቀዶ ጥገና ማድረጋቸውን ይናገራሉ። አረጋዊነታቸው የጤና እክላቸውና አቅመ ደካማነታቸው ከህወሓት ጁንታዎች ዓይን አላዳናቸውም። ዘራፊው ቡድን በዝርፊያና በአፈና ለኖረበት ስልጣኑ ማራዘሚያ ይሆኑ ዘንድ ሚሊሻ በሚል ስም አስታጥቆ መከላከያ ሰራዊትን ይወጉ ዘንድ ላካቸው።

‹‹ይህ ዘመኔ ውጊያ የማደርግበት ሳይሆን የምጸልይበትና የማስታርቅበት ነበር፤ በዚህ እድሜዬ በማይጠበቅ ቦታ መገኜቴ ይጸጽተኛል ይላሉ” አቶ መብራቱ። የሚሊሻ አባል የሆኑት ፈልገው ሳይሆን ታጥቀው ካልተዋጉ የሚከፈላቸው የጡረታ ደሞዝ እንደሚቆምባቸው በጁንታው ማስፈራሪያ ስለተሰጣቸው እንደሆነ ይናገራሉ።

“ደመወዜን አታገኝም በመባሌ ነው ወደ ሚሊሻው የተቀላቀልኩት። ልክ እንደእኔው ሁሉ መሳሪያ የያዙ በሙሉ እንዲዋጉ ተገድደዋል›› ይላሉ አቶ በሪሁን፡፡ ለጥበቃ ስራ የተሰጣቸውን ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ለጁንታው ታጣቂዎች ሰጥተው እርሳቸው ሚንቶፍ ይዘው እንዲዋጉ መደረጋቸውን አዛውንቱ ይናገራሉ፡፡

የመዋጋት ፍላጎትም አቅምም የለኝም ያሉት እኚህ አዛውንት፤ ያገኙትን አጋጣሚ ተጠቅመው ከመሰሎቻቸው ጋር ጠፍተው እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሰራዊት ሰጥተዋል፡፡
ቀሪ እድሜያቸውን ለልጆቻቸው፣ ለልጅ ልጆቻቸው እና ለአገራቸው በጸሎት ማገልገል ምኞታቸው መሆኑን አዛውንቱ አባት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *