በአገራችን የህወሓት አደጋ በሕዝብ ጫንቃ በመጫን የኤርሚያስ ለገሰን ያህል አሉላ ሠለሞን አልበደለንም፡፡ (ግርማ ሰይፉ)
By: Date: November 24, 2020 Categories: የግል እይታ

በዚህ ውይይት የሚነሱ ሃሳቦች የኢትዮ 360 አቋም ሳይሆን የተወያዮቹ ናቸው፡፡ ይሉሃል፤ ኢትዮ 360 አቋም ማን እንደሚነግረን ሌላ ቀን በሌላ መስመር ይነጉርናል ብለን እንጠብ ቃለን፡፡ ለማንኛውም በኖቬምበር 22 በነበራቸው ውይይት ማጣፈጫቸው እኔ ነበርኩ፡፡ መቼ የኢትዮ 360 አቋም ሰላልሆነ በግል ያነሱትን ጉዳይ በግል ምላሽ መሰጠት ተገቢ ይመስኛ ል፡፡ አካፋን ደግሞ አካፋ ማለት ተገቢ ነው፡፡

ወዳጄ ሀብታሙ ያነሳው ጉዳይ መነሻ ያለው ነጥብ ነው፡፡ በነበረው የትግል ሥልት ልዩነት የሃሳብ ልዩነቶች ነበሩ፡፡ ሁሉም እንደሚያወቀው ሀብታሙ የራስህን ሃሳብ ድራማታይዝ አድርጎ ማቅረብ ይችልበታል፡፡ መፅኃፉ ላይ ያሉት ታሪኮች፤ ከባለታሪኮቹ የሰማናቸው ሰዎች በድጋሚ ሀብታሙ ሲያወራቸው አስደማሚ ይሆናሉ፡፡ ይህን በዚሁ እናልፈዋለን

ክፍት አፉ ኤርሚያስ የተከበሩ እያለ ይስድበኛል፡፡ እኛ ሰፈር አንቱ ብሎ ስድብ የለም፡፡ ኤርሚያስ ለገሠ ተው የሚለው ካላገኘ በሂሣብ ትምህርት ያጠናው ሎጂክ ብቻ ሳይሆን ነውር የሚባለው ጭምር የጠፋበት ይመሰለኛል፡፡ በሽታው ግን ጥንቆላ ጭምር ሳያክልበት አልቀረም፡፡

በጭንቅላቴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ሊገምት ይሞክራል፡፡ አሜሪካ ተደብቆ የትግራይን ሕዝብ በጅምላ ለመፈረጅ በሚያስችል ደረጃ ሲንቀሳቀስ የነበረ ፈሪ ዛሬ እኔን ሊከስ መሞከሩ ትዝብት ላይ ሊጥለው እንደሚችል አለመገመቱ የሂሰብ ትምህርት የሰጠውን አዙሮ ማየት ደፍኖበታል፡፡ ኤርሚያስ በዚህ ደረጃ ሊዘቅጥ ይችላል ብዬ ሀስቤ አላውቅም፡፡ ከአሉላ ሠለሞን ጋር መገናኘት ሀጥያት ከነበር በወቅቱ ነበር “ልክ አይደለም” ማለት የሚገባው ዛሬ ምን ፍለጎ እንዳነሳው ያጨሰው ጋንጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ደሮም ቢሆን ልክ ሊሆን አይችልም፡፡

የህወሓት አባሎችን እንዲሁም አሸከሮች ጋር መነጋገር፤ መወያየት ዛሬ እርሱ እየሰበከ፤ እኔን የዛሬ ሶሰት ዓመት ለምን ከአሉላ ጋር ተገናኘ ብሎ ሊከሰኝ ይሞክራል፡፡ ይህ ክፋት ከሆነ የህወሓት አሸከር ከነበረው ከኤርሚያስ ለገሠ ጋር ብዙ ዳገት ወጥተን ወርደናል፡፡ በአገራችን የህወሓት አደጋ በሕዝብ ጫንቃ በመጫን የኤርሚያስን ያህል አሉላ ሠለሞን አልበደለንም፡፡ ከኤርምያስ ጋር ፓስታ መብላት ብቻ ሳይሆን እንደ ነብሱ የሚወደውን ጥቁር ቢራም ጠጥተናል፡፡ ዛሬ የሚፈነጭበትን መረጃ ቲቪ ባለቤት ከሆነው ግርማ ካሳ ጋር እርሱ ሊያየው በሚጠየፍበት ወቅት እኔ በየሬስቶራንቱ እንገናኝ ነበር፡፡ ግርማ ካሳ ዛሬ ወዳጅህ ስለሆነ ልትጠይቀው ትችላለህ፤ ከአሉላ ሠለሞን አይደለም፤ ከሌሎች ብዙ ህወሓቶች ጋር መድረክ ፈጥሮ ውይይት አድርጊያለሁ፡፡ ይህ መቼም የሚያስከስስ መሆኑን እስከዛሬ አላወቅኩም፡፡ ወደፊትም የሚያስከስስ እንደማይሆን አውቃለሁ፡፡ የድድብናው ጥግ ደግሞ፤ እርሱ ዲሲ ቁጭ ብሎ ሊያናገረው ያልቻለውን አሉላ ሠለሞንን እኔ ከአዲስ አበባ መጥቼ ማናገሬን ነውር ማድረጉ ነው፡፡ ዛሬ መቀሌ ከመሸገው ቡድን ዋናዎቹ ህወሓቶች ከላይ እስከታች አግኝቼ አውርቻለሁ፡፡ ይህ እንዴት ሀጥያት ሊሆን ይችላል?

የአህምሮዬን ልክ እንደሚያውቅ ሁሉ አፉን ሳያደናቅፈው ሲቀደድ ነበር፡፡ መቼም ከዚህ በፊት አብረን ባደረግናቸው ውይይቶች የሰጠውን አስተያየት ማንም ዞሮ አያይም ብሎ በመገመት ሊሆን ይችላል፡፡ ቢያንስ በህዝብ ፊት በአደባባይ መፅሃፌን ሲገመግም የተናገረውን እንዴት ሊረሳው ይችላል? እርሱ ፈርቶ የሸሻቸውን ጌቶቹን እኔ በመፅኃፍ ሀጥያታቸውን ስፅፍ፤ እንደርሱ ተደብቄ አልነበረም፡፡ ደግነቱ ፈሪ አላለኝም፡፡

በመጨረሻም በዚህ ሰሜት ይህን መልስ እንድፅፍ ያደረገኝ ዋና ቁምነገር ግን ግርማ “ለትግራይ ሕዝብ እርዳታ አይሰጥ አለ” ብሎ ያለው ነገር ነው፡፡ ይህ ውሻ! እኔ እንደ እርሱ ሆዴን ለመሙላት ዩቲዩብ በመሸቀል አገር የማምስ እንዳልሆንኩ ያውቃል፡፡ ነገር ግን ህወሓት በሰብዓዊነት ስም እንዳያንሰራራ በር መዘጋት አለበት በሚል የሰጠሁት አስተያየት የህወሓት ትንፋሽ ሰለሚያሳጥር፤ የእርሱም ትንፋሽ ሰለሚያጥር በንዴት ተነስቶ እንደሆነ ለመረዳት አያስቸግረም፡፡ ሆዳም ሰው፤ ሁሉ ለሆዱ የሚያድር ይመስለዋል፡፡

“እርዳታ መቆም የለበትም፤ ህወሓት ነብስ እንዳይዘራ እንጠንቀቅ” በሚል የሚሰጥ ሀሣብ የሚያበሳጫው ቢኖር ከህወሓት ጡት የሚጠባ ብቻ ነው፡፡ ሌላው የሚገርመው ይህ ንፍጣም ባገኘው አጋጣሚ የሚሰድበውን ፓርቲ በምን ጉዳይ አቋም ሊወስድ እንደሚገባው ሊመክር ይዳዳዋል፡፡ መግለጫ ፅፉ ለሚልክላቸው ይህን ማድረግ ይችላል፡፡ ለአብይም ምክር ቢጤ ለግሶታል፤ “አንገቱን አንቀህ ከባሱ ማውጣት አለብህ!” በሚል፡፡ ግድ የለም፤ ከእኔ እና ካንተ ለትግራይ ህዝብ በሰብዓዊነት ጉዳይ ማን ቅርብ እንደሆነ፤ በተግባር እንፈተሻለን፡፡ ለማንኛውም ግን በሚዲያ ማቀርሸትህን ብትተው ጥሩ ነው መትፋት ያስነውራል፡፡ (አቶ ግርማ ሰይፉ በኢትዮ 360 ለቀረበባቸው ክስ የሰጡት ምላሽ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *