ህወሃቶች ትናንት ቀብረነዋል፣ አንገቱን አስደፍተነዋል እያሉ ሲዘባበቱበት የነበረውን አማራ እግሩ ስር ወድቀው መለመን ጀምረዋል። ዛሬ በእንግሊዝኛ በጻፉት መግለጫ ላይ “ ደጉ የአማራ ህዝብ ሆይ ተፍጥሯዊ ወዳጅህንና ጠላትክን እንድትለይ እንጠይቅሃለን። የትግራይ ህዝብ የአማራ ጠላት አይደለም። የአማራ ጠላት ራሱን ለማንገስ የሚሯሯጠው ፋሽስቱ አብይ አህመድ ነው። የአማራ ህዝብ በትግራይ ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተቃወም።” ብለዋል።

የአማራ ህዝብ ተፈጥሯዊ ጠላት የሚሉት ኦሮሞውን ነው። ያሳዝናል። ጊዜ ደጉ ግን ስንቱን ያሳየናል። ለማንኛውም አማራ ወዳጅ ህዝብ እንጅ ጠላት ህዝብ የለውም። አንድ ህዝብ ለሌላው ህዝብ ጠላት ሆኖ አያውቅም፤ ሊሆንም አይችልም። ተፈጥሯዊ ወዳጅና ተፈጥሯዊ ጠላት የሚባል ህዝብም የለም።

የአማራ ህዝብ ከህወሃት ጋር ያለው ቅራኔ የህልውና ነው። የህወሃት መጥፋት ለአማራ ህዝብ ህልውና ብቸኛ ዋስትና ነው። ህወሃት የአማራን ህዝብ ለማጥፋት አልተሳካለትም እንጅ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። አሁን ሁሉም ነገር እያበቃ ነው። አማራ አንገቱን ቀና አድርጓል።

የኦሮሞ፣ ሶማሊ፣ ደቡብ ወዘተ አንገትም ቀና ብሏል። ትግራይም በቅርቡ አንገቱን ቀና ያደርጋል። አንዱ ሌላውን በጠላትነት የማይፈርጅበትና ሁሉም አንገቱን ቀና አድርጎ በኩራት የሚራመድበት የፖለቲካ ስርዓት ይመሰረታል። የጠላትነት መንፈስ በአንድነት መንፈስ ይተካል። ድል ለህልውናቸውና ለነጻነታቸው ለተዋደቁት ሰማዕታት ሁሉ። ፋሲል የኔ አለም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *