የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ ማስጠንቀቂያ አለመስጠቱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ አረጋግጠዋል ሲል ራሱ ዶይቼ ቬለ ዘገበ። ዋና ዳይሬክተሩ በዶይቼ ቬለ ዘገባዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አሉት ያሏቸውን ቅሬታዎች ግን በዝርዝር አስረድተዋል።

ባለሥልጣኑ የሬውተርስ የአዲስ አበባ ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ፤ ለዶይቼ ቬለ እና ለቢቢሲ ራዲዮ ጣቢያዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ የሚል መረጃ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተሰራጭቶ ነበር። መረጃው የተሰራጨው የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ለሸገር ራዲዮ ጣቢያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ መሠረት በማድረግ ነው።

“ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው ማስጠንቀቀያ የለም። ምን አልባት ቢሯችን ጠርተን ያደረግንው ምክክር እንደዚያ ተደርጎ ተገልጾ ከነበረ ስህተት ነው። የጽሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ የሚባል ነገር ግን ለዶይቼ ቬለ የሰጠንው የለም” ያሉት ዶክተር ጌታቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በዘገባዎች ላይ ቅሬታዎች እንዳሉት አስረድተዋል።

“ወደ አንድ ወገን ማጋደላችሁ ይኼ ነው ሊባል የሚችል አይደለም። በብዙ ቅሬታ አቅራቢዎች ጭምር የተደገፈ ነው።እኛም ደግሞ በሙያዊ ትንታኔ ያንን አይተን ያንን ቅሬታችንን የምናቀርብ ይሆናል። በዚህ አይነት ከቀጠለ ሌሎቹን ተጠያቂ እንዳደረግንው ሁሉ ዶይቼ ቬለ በዚያ መልኩ አይጠየቅም ማለት አይቻልም” ሲሉ ተቋማቸው ያለውን ቅሬታ ዶክተር ጌታቸው አስረድተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *