የትህነግ እኩይ ኃይል ያልጠበቀው አስገራሚ ኦፕሬሽን!

የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት ከታጠቃቸው ግዙፍ መሳሪያዎች መካከል 𝟖𝟎% ታጥቆ ትግራይ ክልል የነበረው ሰሜን እዝ ነበር፤ በተቀረው የመከላኪያ ሰራዊት እዞችና ክፍለጦሮች ውስጥ የነበረው ትጥቅ 𝟐𝟎% ብቻ ነው

➦ ዶ/ር አብይ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከመጣ በዃላ ከኤርትራ ጋር የገባውን እርቅ አስከትሎ እነዚሁን ግዙፍ የጦር መሳሪያዎች ከትግራይ ክልል ቀንሶ ለማውጣት ሞክሯል፥ ነገር ግን ሳይሳካለት ቀርቷል፤ በዋናነት ህውሓት ህዝቡን በሻቢያ ሊያስወርረን ነው ፕሮፖጋንዳ ህዝቡ መከላኪያው ከክልሉ በከፊል ለመውጣት ያደረገውን ሙከራ አውራጎዳና ላይ በመተኛት ሳይቀር አስተጓጉለውት ቆይተዋል፤

➦ የህወሓት እቅድ የነበረው ፦ በትግራይ ክልል ለረጅም ዓመታት የተከማቸውን የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት ከበባድ መሳሪያና ትጥቅ በአሳቻ ሰዓት በመዝረፍ የክልሉን ልዩ ሀይል አስታጥቆ አይነኬ፥ ምን አልባትም ፌደራል መንግስቱን በነጠቁት መሳሪያ ለመጣል ታልሞ ነበር፤

➦ በህውሓቶች እሳቤ ቃልበቃልም ”አብይ ያለው መከላኪያ ሰራዊት አቅሙ ከሚሊሻነት ያነሰ ነው…” ይሉት የነበረው እሳቤ ሰሜን እዝ የታጠቀውን ለመንጠቅ ገፋፍቷቸዋል፤

➦ ህውሓት የነበረውን እቅድ ከሳምንት በፊት ባልታሰበ ሰዓት ተግባሪዊ ወደ ማድረግ ገባ (በርግጥ ያልታሰበ የምንለው ለኛ ለተራ ዜጎች እንጂ ለመንግስት እንደማይሆን እርግጠኛ ነኝ) ፤

➦ህውሓት የሰሜን እዝን ትጥቆች ከተራ 𝐀𝐊-𝟒𝟕 ጀምሮ እስከ ቡድን መሳሪያ 𝐑𝐏𝐆፣ ከ𝐙𝐔-𝟐𝟑 እስከ በረት ለበስ 𝐓𝐚𝐧𝐤 እስከ 𝐁𝐌 𝟐𝟏፣ ከ 𝐌𝐢𝐧𝐢 𝐌𝐢𝐬𝐬𝐢𝐥𝐞 (𝐌𝐇𝐓𝐊) እስከ 𝐒-𝟏𝟐𝟓 𝐏𝐞𝐜𝐡𝐨𝐫𝐚 𝐌𝐢𝐬𝐬𝐢𝐥𝐞 … ወዘተ የመከላኪያ ሰራዊት ትጥቅ ዘርፈው ታጠቁ። ህውሓት ከሰሜን እዝ ዛይ ሀንግ ሰርታ በታጠቀችው መሳሪያ አይደለም የተቀረውን የኢትዮጵያ ክልሎች ይቅርና ምስራቅ አፍሪካ ላይ ያሉ ሀገሮችን ማንበርከክ ያስችላት ነበር። ዶ/ር አብይ በብርሃን ፍጥነት ቀድሞ እጇ ላይ እንዳለ አመድ አደረገባት እንጂ።

🚫 ዘርፈው የታጠቁት ዋናዋናዎቹ በሁለትናሶስት ቀናተ እንዲወድሙ ተደረገ። እንዴት❓

➦የመጀመሪያው አስምሽኔ ያለፉትን ሁለት ዓመት የዶ/ር አብይ መንግስት 𝐓𝐏𝐋𝐅 በተለያዩ ክልሎች በምትሰጠው የቤትስራ እረፍ አጥቶ መስራት ያለበትን የሰራ ባይመስልም በሚገባ መከላኪያ ሰራዊቱን ውስጥ ለውስጥ እየሰራበት እንደነበር በርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ለዚህ አንዱ ማረጋገጫ አድርጌ የማቀርበው 𝟖𝟎% ትጥቅ የተሸከው ሰሜን እዝ ተመቶበትና ከባባድ መሳሪያዎቹ ተዘሮፈውና በሌላ አካል ትጥቅ ስር ገብተው ዶ/ር አብይ የሚመራው መከላኪያ ሰራዊት በተቀረው አቅሙ ገጥሞ 𝐒𝐮𝐫𝐯𝐢𝐯𝐞 ከማድረግ በላይ ድል ማድረጉ ሲሆንና የህውሓት ጀነራሎች በሞሉበት የመከላኪያ ሰራዊት አደረጃጀት ድምጹን ሳያሰማ 𝐔𝐂𝐀𝐕 / 𝐔𝐧𝐦𝐚𝐧𝐧𝐞𝐝 𝐂𝐨𝐦𝐛𝐚𝐭 𝐀𝐫𝐞𝐚𝐥 𝐕𝐞𝐡𝐢𝐜𝐥𝐞𝐬 ወይንም 𝐂𝐨𝐦𝐛𝐚𝐭 𝐃𝐫𝐨𝐧𝐞𝐬 ማስታጠቁ ነው።

ሌላው መቀሌ አየር ሀይል ጊቢ የነበሩትን 𝐒𝐮𝐤𝐡𝐨𝐢 𝐒𝐮-𝟐𝟕 𝐑𝐮𝐬𝐬𝐢𝐚 ሰራሽ የጦር ጀቶችን ባለፉት ሁለት ዓመታት 𝐒𝐨𝐟𝐭𝐰𝐚𝐫𝐞 ሲስተማቸው 𝐔𝐩𝐝𝐚𝐭𝐞 እንዳይሆን በማድረግ ከአገልግሎት ውጪ ማድረጉ ነው።

➦ዶ/ር አብይ 𝐂𝐀𝐈𝐆 𝐖𝐢𝐧𝐠 𝐋𝐨𝐨𝐧𝐠 𝐃𝐫𝐨𝐧𝐞 መከላኪያ ሰራዊቱን ማስታጠቁ በ 𝐑𝐮𝐦𝐨𝐮𝐫 ደረጃ ሲነገር ቢቆይም ፥ በርግጥም መከላኪያው ህውሓት የዘረፋቸውን ከባባድ መሳሪያዎች ያለከልካይ እየሄደ ሲደበድብ አረጋግጧል።

እንዴት በቀላሉ ሊወድሙ ቻሉ?
➦ በመጀመሪያ ቀን ድብደባ ኢላማ የተደረገው ኩዊኻ ያለውን ቀደሞ የመከላኪያ ሰራዊት የነበረውና ህውሓት የዘረፈውን የ 𝐑𝐀𝐃𝐀𝐑 𝐒𝐲𝐬𝐭𝐞𝐦 ማውደም ነበር፥ ተሳካ። ህውሓት ይሄን 𝐑𝐚𝐝𝐫 ተማምና በሰዓታት ውስጥ ክልሉ ላይ በረራ አግዳ እንደነበር የሚታወስ ነው።
➦ 𝐑𝐚𝐝𝐚𝐫 ሲስተሙ መውደሙን ተከትሎ ከ 𝐉𝐞𝐭 𝐇𝐞𝐥𝐢𝐜𝐨𝐩𝐭𝐞𝐫 እስከ 𝐌𝐢𝐥𝐢𝐭𝐚𝐫𝐲 አውሮፕላኖቻችን ያለ ከልካይ ክልሉን ተቆጣጠሩት።
➦ ሌሎች ግዙፍ መሳሪዎች ከሰሜን እዝ ተዘርፈው በፍጥነት የተለያየ አካባቢ ላይ እንዲበታተኑ የተደረጉ መሳሪያዎችን የማውደሙ ተግባር ዶ/ር አብይ ያለፈው ዓመት የገዛው ድሮን ተቆጣጠረ።

ይህ ድሮን:-

➽ በአየር ላይ በአንዴ ቻርጅ 𝟑𝟐 ሰዓታትን መቆየት ያስችለዋል። ይህም ለተከታታይ ሰዓታት ኢላማውን አድኖ መምታት አስችሎታል፤

➽ የተገጠመለት 𝐃𝐚𝐲 𝐋𝐢𝐠𝐡𝐭 (በብርሃን የሚቀርጽ) እና 𝐈𝐧𝐟𝐫𝐚𝐫𝐞𝐝 ( 𝐍𝐢𝐠𝐡𝐭 𝐕𝐢𝐬𝐢𝐨𝐧 በጨለማ የሚቀርጽ) ካሜራ ኢላማውን ከመምታቱ አስቀድሞ በሚገባ የ 𝐒𝐮𝐫𝐯𝐞𝐢𝐥𝐥𝐚𝐧𝐜𝐞 ስራ እንዲሰራ አስችሎታል፤

➽ የብዙዎች ጥያዌ የሚሆነው ህውሓት የሰረቀችውን መሳሪያ ከእይታ ውጪ በሚሆን ቦታዎች መደበቅ አትችልም? ነበር የሚል እንደሆነ አልጠራጠረም። ትክክል ነው መደበቅ ይችላሉ። ችለውማል። ነገር ግን ሁሉም በሚባል ሁኔታ እየተለቀሙ ተመተዋል። እንዴት? ድሮኑ 𝐌𝐞𝐭𝐚𝐥 𝐚𝐧𝐝 𝐌𝐢𝐥𝐢𝐭𝐚𝐫𝐲 𝐞𝐪𝐮𝐢𝐩𝐦𝐞𝐧𝐭 𝐃𝐞𝐭𝐞𝐜𝐭𝐨𝐫 𝐒𝐞𝐧𝐬𝐨𝐫𝐬 አሉት። ይህም ግዙፍ የሚሊተሪ መሳሪያዎችን አነፍንፎ ያሉበት ድረስ በመሄድ ማውደም አስችሎታል።

ህውሓት እጅ ላይ ያሉት አብዛኛዎቹ ሮኬቶች እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ወደምዋል። ጥቂት የተረፉ በተለይም በየ ዋሻ ውስጥ የሸሸጓቸው ሮኬቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ተኩሰው ጉዳት ሊያደርሱ ይችሉ ይሆናል። ቢሆንም 𝟐𝟒/𝟕 በክልሉ ሰማይ ላይ ድሮኖቹ የ 𝐒𝐮𝐫𝐯𝐞𝐢𝐥𝐥𝐚𝐧𝐜𝐞 ስራ በመስራት ላይ በመሆናቸው ብዙሃኑን ጥቅም ላይ ለማዋል ከመሞከሩ በፊት ይመታል። (ሰብለ መኮንን)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

//thaudray.com/4/4057774