By: Date: November 18, 2020 Categories: ትንታኔ

ህወሃቶች ክ27 አመታት በላይ ብዙ ግፍና ሰቆቃዎች የፈጸሙ ናቸው። ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ በይቅርታ መንፈስ አልፏቸው ነበር። ለውጥ መጣ የተባለው ከራሱ ከኢሕአዴግስለነበረ። በዚህ አጋጣሚ እነ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ አባይ ጸሃዬ በሰላም ለወጣቶች ሃላፊነቱን አስረክበው ገለል ቢሉ ጥሩ ነበር። ሕገ ወጥ ምርጫ ሲያደርጉ ይቅር ተባሉ።

ምርጫው እንዳልተደረገ ይቆጠራል ተብሎ። ከስልጣን ዉረዱ አልተባሉም። ምን ችግር ነበረው እንደገና ለመጪው ምርጫ እንሳተፋለን ቢሉና ነገሮችን ለማብረድ ቢሞክሩ ኖሮ ያንን እንዲያደርጉ ብዙ ጻፍን፣ ተመጻንን፣ ግፊት አደረግን።

በጣም የሚገርማችሁ እንደሚሸነፉ ነግረናቸዋል። ሚሊሺያዎች ተገደው ስለሆነ አይዋጉላችሁም። “ከላይ በኤርትራ ከታች በጎንደር፣ በወሎና በአፋር ተከባችሁ፣ ዉሃ ነዳጅ፣ ምግብ በአጠቃላይ ስንቅ ችግር ያጋጥማቹሃል። በመሳሪያና በሰው ኃይል ብቻ ጦርነትን ማሸነፍ አትችሉም። መሸነፋችሁ አይቀርም” ብለናቸው ነበር።

ግን ሰዎቹ ግትር ሆኑ። ማስተዋል ተሳናቸው፡፡ በልዩ ኃይላቸውና በመሳሪያቸው ተመኩ። ከደርግ መማር ተሳናቸው። የፌዴራል መንግስቱን ጎትተው ጦርነት ውስጥ አስገቡት። አሁን ከሕወሃት ጋር የሚደረገው ውጊያ 2 ሳምንት ሆኖታል። ብዙ ወገኖች ሞተዋል፡፡ ብዙዎች ተፈናቅለዋል።ብዙ ውድመቶች ተከስተዋል። በጣም ያሳዝናል። ይሄ ሁሉ መሆን አልነበረበትም። በጣም ልብን ያደማል። ህወሃት በሰሜን፣ ኦነግ በምእራብና በደቡብ አገራችንን አመሷት።

በዚህ ሁለት ሳምንት በተደረገው ዉጊያ ወልቃይት ጠገዴ ካፍታ ሁመራና ራያ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ክሕወሃት ነጻ ወጥተዋል። አልፎ አልፎ አንዳንድ ቦታዎች ገና ያልጠሩ ቢሆንም። በአሁኑ ወቅት መከላከያ ወደ መቀሌ እየገሰገሰ ነው። መቀሌ በአምስት አቅጣጭ መግባት ይቻላል፡

ከአዲግራት በዉቅሮ አድርጎ ከሰሜነ ወደ ደቡብ በመጓዝ በአሁኑ ወቅት በዉቅሮ ዉጊያ እንዳለ እየተሰማ ሲሆን፣ ጄ/ር ታደሰ ወረደ፣ በአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጊዜ ምክትል ኢታ ማጆር ሹም የነበሩት፣ መከላከያን ክደው ለሕወሃት ሲዋጉ አዲግራት ላይ ክፉኛ ቆስለው መማረጃቸውን እየሰማን ነው። ዉቅሮ ከመቀሌ 42 ኪሎሚተር ብቻ ነው የምትርቀው
ከአላማጣ በመኾኔ በኩል መኾኔ በፌዴራል ስር ስትሆን ከመቀሌው 101 ኪሎሜትር ትርቃለች። በአላማጣውም መስመር እጅግ በጣም ብዙ የትግራይ ታጣቂዎች እጅ ሰጥተዋል።

ተግደው ስለተሰማሩ አጋጣሚውን ባገኙ ቁጥር እያመለጡ ነው ከአማራ ክልል ከሰቆጣ በሰምሬ በኩል (ከሰምሬ መቀሌ 54 ኪሎሜትር ነው) ከአፋር ክልል በአባላ በኩል ከአባላ መቀሌ 43 ኪሎሜትር ነው በሃገረ ሰላም በኩል ከአቢ አዲ(ተንቤን) መቀሌ (በሃገረ ሰላም ትልቅ የወያኔ ሚስጥራዊ እዝ ያለበት ዋሻ ነው። ምን አልባትም መቀሌ ከተያዘ ወደዚህ ዋሽ ሊመጡ ይችሉም ይሆናል።፡

እንግዲህ የሕወሃት ሰዎችና ደጋፊዎች፣ “ትንሽ ለድሃው የትግራይ ወጣት የሚያስብ እንጥብጣቢ ርህራሄ ካላችሁ እጅ ስጡ። ጦርነቱን አቁሙ። በተለይም መቀሌን እንዳትያዝ ዉጊያ ካደረጋችሁ መቀሌ ልትወድም ትችላለች። ለ28 አመታት ያለማችኋትን ከተማ እንድትወድም አትፍቀዱ” እላቸዋለሁ።

ደግሚ እላለሁ ማሸነፍ አይደለም መመከት እንደማይቻል አውቀው፣ ከዚህ በኋላ ደግሞ የበለጠ ደም እንዳይፈስ እጅ ይሰጡ ዘንድ ለነዚህ ሰዎች ቀረቤታ ያላችሁ፣ ከነርሱ ጋር የምትገናኙ ፣ በተለይም የትግራይ ልሂቃን ክፈተኛ ጥረትና ማግባባት ታደረጉ ዘንድ እጠይቃለሁ። ቢቻል ከዚህ በኋላ ደም ባይፈስ ጥሩ ነው። እጅ ይስጡ። (ግርማ ካሳ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *